የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው፣ የአፍሪካ አገራት የአውሮፕላን በረራ ገደቦችን እንዲያላሉ ጠየቁ።መስፍን፣ በአየር መንገዶች መካከል ጠንካራ ውድድር እንዲኖር ለማበረ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/n_b00cJOm1nZn-JEHQH15YcuB5TTl3Jd7-v6OQchvBpAPZMAEVAkl527JcmWYL5m49X1N5VFFrIjWFw7V94SaZsOcdwqubmujPN_zYMKtbmsM1MQo7xqIZhJ3uj9Kc5_cTEyUWmpDbBogTQBNSo9e13pBl-DKLjovnrbdpDX9MuIhZzW8sWOfwRvYOKKBpVg2ubKE2KXt5KaqgI4jkYnhaSz1EZlKUx7UglMaUZwj1aGCjAC29fSYBptVRVWs9vCJSx775srmasYqsEsDpXo1ChaZpRGV0lmuhs9BwzzJSNOAoD0CQub_Y_3yU28Bs8IdCVKiemx4hNwXau07tvmPg.jpg

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው፣ የአፍሪካ አገራት የአውሮፕላን በረራ ገደቦችን እንዲያላሉ ጠየቁ።

መስፍን፣ በአየር መንገዶች መካከል ጠንካራ ውድድር እንዲኖር ለማበረታታትና የአውሮፕላን መንገደኞችን የትኬት ዋጋ ለመቀነስ፣ ኹሉም አየር መንገዶች በአሕጉሪቷ የአየር ክልል በነጻነት እንዲበሩ እንዲደረግ መጠየቃቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

መስፍን፣ የበረራ ገደቦች የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በርካታ አየር መንገዶች መዳረሻቸውን ለማስፋት በሚያደርጉት ጥረት ላይ እንቅፋት ደቅነዋል በማለት ተናግረዋል ተብሏል።

37 የአፍሪካ አገራት የበረራ ገደቦችን ለማላላት ስምምነት የፈረሙት ከአምስት ዓመት በፊት ቢኾንም፣ እስካኹን በአሕጉሪቱ አንድ ነጻ የአየር ትራንስፖርት የበረራ ቀጠና መፍጠር አልተቻለም ሲል ፋይናንሻል ታይምስ ጋዜጣ ዘግቧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 19 ቀን 2016 ዓ.ም
ፎቶ–ፋይል

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply