You are currently viewing የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ከኃላፊነታቸው ለቀቁ። በምትካቸው አቶ ግርማ ዋቄ ተሹመዋል! የአማራ ሚዲያ ማዕከል  መጋቢት 14 2014 ዓ/ም አዲስ አበ…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ከኃላፊነታቸው ለቀቁ። በምትካቸው አቶ ግርማ ዋቄ ተሹመዋል! የአማራ ሚዲያ ማዕከል መጋቢት 14 2014 ዓ/ም አዲስ አበ…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ከኃላፊነታቸው ለቀቁ። በምትካቸው አቶ ግርማ ዋቄ ተሹመዋል! የአማራ ሚዲያ ማዕከል መጋቢት 14 2014 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ… ዓየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ አቶ ተወልደ በፈቃዳቸው ከሀላፊነት መልቀቃቸውን አስታውቋል።አየር መንገዱ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፥ አቶ ተወልደ ላለፉት ስድስት ወራት ህክምናቸውን በአሜሪካ ሲከታተሉ መቆየታቸውን አስታውሷል፡፡ አቶ ተወልደ ገብረማርያም በግል የጤና እክል ምክንያት የአየር መንገዱ ዋና አስፈጻሚ ሆነው መቀጠል እንደማይችሉ በመግለጽ የስራ አመራር ቦርዱ የስራ መልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል ብሏል አየር መንገዱ፡፡ አየር መንገዱ በመግለጫው አቶ ተወልደ ከአንድ አስርት ዓመታት በላይ ተቋሙን በመሩበት ወቅት ከፍተኛ ስኬት ያስመዘገቡ መሆናቸውን አመልክቷል ያለ ሲሆን በእርሳቸው አመራር አየር መንገዱ በሁሉም መለከያ የተለየ ስኬት ማስመዝገቡን በመጠቆምም ዓመታዊ ገቢው ከ1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ተነስቶ አሁን ላይ ከ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር መብለጡን ጠቁሟል። 33 የነበሩት የአውሮፕላን ቁጥሮችም ወደ 130 ማደጋቸውን እና በዓመት የሚያስተናግደው የመንገደኞች ቁጥር ከ3 ሚሊየን ወደ 12 ሚሊየን ከፍ ማለቱን አስታውቋል። ከአቶ ተወልደ ስራ መልቀቅ ጋር ተያይዞም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ለብዙ ዓመታት ያገለገሉት አቶ ግርማ ዋቄ የአየር መንገዱ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መሾማቸውን አየር መንገዱ ገልጿል፡፡ አቶ ግርማ ዋቄ አየር መንገዱን ለሰባት ዓመታት በመምራት ለዕድገት እንዲበቃ መሰረት ጥለዋል ያለው አየር መንገዱ በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ የስራ ልምድ ያላቸውና በዘርፉ ስኬታማ መሪ መሆናቸው በመመልከት መሾሙን አስታውቋል። አቶ ግርማ ዋቄ የአየር መንገዱ የስራ አመራር ቦርድ ሆነው መሾማቸው አየር መንገዱን ለበለጠ ስኬት ሊያበቁ የሚችሉና ተቋሙ ወደፊት ከሚጠበቅበት የዕደገት ደረጃ ሊያደርሱት እንደሚችሉም የታመነ መሆኑንም አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply