የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2020 የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ ሆነ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2020 የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17 ቀን 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢዝነስ ትራቭሌር አዋርድ የ2020 የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ በመሆን ተሸለመ።
ይህ ሽልማት በቢዝነስ ትራቭለር መፅሄት በኩል ነው ይፋ የሆነው።
የመፅሄቱ አንባቢዎች በሰጡት ድምፅ እና በገለልተኛ የጥናት ተቋም በተሰጠ ውጤት ይህ ሽልማት ለኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደተበረከተ ነው የተነገረው።
ከፈረንጆቹ ሚያዝያ ወር 2020 እስከ ሰኔ 2020 ድረስ በተካሄደ ግምገማ መሰረት የተሰጠ ሽልማት መሆኑን መፅሄቱ አስታውቋል።

The post የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2020 የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ ሆነ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply