የኢትዮጵያ አየር መንገድ 6ኛ የአሜሪካ መዳረሻ በረራውን መጀመሩን አስታወቀ።አንጋፋው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሜሪካ 6ኛ መዳረሻው ወደሆነው አትላንታ ግዛት በረራ አስጀምሯል።የአሜሪካ በረ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/peN-X-CMfEm6nZVvdo479g2cba046-BXSJoLCELL20KxdCjTXPKJ7SzPebmAIQ3q5XqsnmS41wzdgtm0ieIKJ3P1bFbkR9Ug7uj5h5ikvNFHP9JPEPDlYkN6gIvxMIF5fMFdL8h0aE3gZvlquD_dbXt3XMzg1J-Ela2_xKfjXSLFJJDxxkNRVC4W-Jro4Ro4jgTniVRtaUMoNtUmmyYTzueaip62dNsh7rV70OVda-c-d_Sp36r0A6hYY3BO3v3O90S7li_4tQgU4oxHvrINCWMkVVl0fTrvfsUJG6M80S85v9K_bPo6U3m-VHLOGDIhw80eKLaoj3u6ghCVPDz5TQ.jpg

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 6ኛ የአሜሪካ መዳረሻ በረራውን መጀመሩን አስታወቀ።

አንጋፋው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሜሪካ 6ኛ መዳረሻው ወደሆነው አትላንታ ግዛት በረራ አስጀምሯል።
የአሜሪካ በረራውን በዋሽንግተን እና በኒውዮርክ የጀመረው አየር መንገዱ ስድስተኛውን የበረራ መዳረሻው አትላንታ አድርጓል።

ይህም በአትላንታ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሃገራቸው በቀጥተኛ በረራ መጠቀም እንደሚያስችላቸው እና እንግልቱን እንደሚቀንስላቸው ተገልጿል።
በበረራው ማስጀመሪያ መርሃግብር ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ከንቲባ ወ/ሮ አደነች አቤቤ የበረራ መዳረሻዎችን ማስፋት የሁለቱን ሃገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያጠነክራል ብለዋል።

ከዚህ ቀደም አየር መንገዱ ዋሽንግተንን እና ኒዎርክን ጨምሮ በቺካጎ ፣ኒዮርክ እና ሚያሚ በረራዎችን ያደርግ ነበረ ተብሏል።

ወደ አትላንታ ባደርገው የመጀመሪያ በረራም ቦይንግ 787-9 ዘመናዊ አውሮፕላን ጥቅም ላይ አውሏል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለምአቀፍ መዳረሻዎቹን 133 ያደረሰ ሲሆን 134ኛውን ደግሞ በቀጣይ ሳምንት እንደሚያስጀምር አስታውቋል።

በመሳይ ገ/መድህን

ግንቦት 09 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Source: Link to the Post

Leave a Reply