የኢትዮጵያ  አዳር በምዕራብ እና በሰሜን (ታህሳስ 19፣ 2013ዓ.ም)  ወለጋ  በተለየ ሁኔታ ሰላም ከራቀው  ሁለት ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ብልፅግና ወለጋ ላይ  ግዛቱ ደካማ ነው፡፡  የወለ…

የኢትዮጵያ አዳር በምዕራብ እና በሰሜን (ታህሳስ 19፣ 2013ዓ.ም) ወለጋ በተለየ ሁኔታ ሰላም ከራቀው ሁለት ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ብልፅግና ወለጋ ላይ ግዛቱ ደካማ ነው፡፡ የወለ…

የኢትዮጵያ አዳር በምዕራብ እና በሰሜን (ታህሳስ 19፣ 2013ዓ.ም) ወለጋ በተለየ ሁኔታ ሰላም ከራቀው ሁለት ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ብልፅግና ወለጋ ላይ ግዛቱ ደካማ ነው፡፡ የወለጋ ብልፅግናዎችም ኦቦ ለማ መገርሳን ጨምሮ ከፖለቲካው ተገፍተዋል፡፡ ብልፅግና እና ወለጋ አይን እና ናጫ ሆነዋል፡፡… በአንድ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ወለጋ መሄድ አልችልም፡፡ ከሄድኩም ልገደል እችላለሁ ሲሉ ተደምጠው ነበር፡፡ በወለጋ ያሉ አራቱም ዞኖች በኩምሳ ዲሪባ ወይም በትግል ስሙ በጃል መሮ ፊታውራሪነት ይመራሉ፡፡ ጃል መሮ የሚመራውን የኦነግ ክንፍ ኦነግ ሸኔ እያሉ የመንግስት ሚዲያዎች ቢጠሩትም፣ ጃልመሮ ግን ኦነግ አንድ ነው፡፡ አዛዥችንም ኦባ ዳውድ ኢብሳ ነው፡፡ የምንታዘዘውም ከአዲስ አበባ ነው የሚል አውድ ያለው ንግግር ለቢቢሲ አማርኛ በአንድ ወቅት ተናግሯል፡፡ ጃል መሮ የአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረ ሲሆን፣ ትምህርቱን አቋርጦ ወደ ጫካ ገብቶ የኦነግን ጦር እየመራ ይገኛል፡፡ እንደ ጃል መሮ ሰው ንፅሃንን የሚገድል እና ተማሪዎችን የሚያፍነው የኦሮሞ ብልፅግና እንጂ ኦነግ አይደለም የሚል ሀሳቡን ቢቢሲ ላይ አጋርቷል፡፡ በእርግጥም በኦሮሚያ ብልፅግና እና በኦነግ መካከል ያለው ያልተሰመረ ግንኙነት ስላለ ማነው ኦነግ? ማነው ብልፅግና የሚለውን ለመለየት ያስቸግራል፡፡ በብልፅግና የሚሰለጥኑ የኦሮሚያ ልዮ ሀይል አባላት በብዛት የኦነግ አባላት ናቸው፡፡ የፖለቲካ አመራሮች የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋና አማካሪ ኦቦ ሌንጮ ባቲ እና የማዕድን ሚኒስትሩ የኦነግ አባል ነበሩ፡፡ እነ ታየ ደንዳዓ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኦነግ ደጋፊ እንደነበሩ ይታወቃል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መረጃ ለኦነግ ያቀብሉ እንደነበር ቢቢሲ በዘገባው አረጋግጧል፡፡ የቀድምው የኦሮሚያ ክልል ሰላም እና ደህነት ሀላፊ የነበሩት ብርጋዴር ጀኔራል ከማል ገልቹ ኦነግ በመንግስት እንደሚደገፍ እና 20 ባንክም የተዘረፈው በመንግስት ነው ሲሉ ለኤልቲቪ ተናግረው ነበር፡፡ በመንግስት እና በኦነግ መካከል ያለው ያልተሰመረ እና መርህ አልባ ግንኙነት ኦሮሚያ ክልል የንፁሃን መገደያ እና መፈናቀያ ቦታ ሆኗል፡፡ አሁን በኦሮሚያ ኦነግ በተለያዮ አካባቢዎች ጥቃት እየሰነዘረ ነው፡፡ የመንግሥት ታጣቂዎች ሳይቀር እየተገደሉ ነው፡፡ ንፅሃንን በጅምላ እየተገደሉ ነው፡፡ የጃል መሮ እናት ከልጃቸው ጋር ግንኙነት አለሽ ተብለው መታሰራቸው በኦነግ በኩል ቁጣን ቀስቅሷል፡፡ የጃል መሮ እናት በእስርቤት ሆነው ክፉኛ እንደታመሙ እና ህክምናም እንደተከለከሉ ኦኤምኤን ዘግቧል፡፡ የጃል መሮ እናት እስር ፣አሁን ያለው መንግስታዊ መበስበስ፣ ወታደሩ በየቦታው መባከኑ ንፅሃንን ለመጠበቅ አስቸጋሪ ስለሚሆን ዜጎች በየአካባቢያቸው ራሳቸውን አደራጅተው እንዲጠብቁ የአሻራ ምልከታ ያሳያል፡፡ በሌላ በኩል የመተከል ጉዳይም ትኩስ ስጋት ያገረሸበት አካባቢ ሲሆን ታጣቂዎች በየጫካው ታጥቀው ለጦርነት ተዘጋጅተዋል፡፡ በመተከል እስካሁን የመንግሥት መዋቅሩ ሙሉ በሙሉ የቆመ ሲሆን፣ በአንዳንድ ወረዳዎች የጤና ጣቢያዎች ሁሉ ዝግ ሆነዋል፡፡ መምህራን፣ የጤና ባለሙያዎች፣ የባንክ ሰራተኞች በተደጋጋሚ በመታፈናቸው ስራቸውን እየለቀቁ ይገኛሉ፡፡ ጤና ጣቢያዎች ያለ ጤና ባለሙያ ቁመዋል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች የመብራት እና የቴሌ አግልግሎት ተቋርጧል፡፡ የትራንስፖርት ስምሪትም የለም፡፡ ችግሩ ተቋማዊ ስለሆነ ተቋማዊ ለውጥ ኢትዮጵያ ትፈልጋለች፡፡ ሱዳንም አማፂያን በመደገፍ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመድፈር እያሴረች እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ ደቡብ ሱዳን በጋምቤላ እና በወለጋ በኩል ከአማፂያኑ ጋር እንዳትገናኝ ያሰጋል፡፡ የብልፅግና ኮልኮሌዎች ይሄን ሁሉ ሀገራዊ ውስብስ ሁኔታ የመረዳትም ሆነ የመፍታት አቅም ሰለሌላቸው ልሂቃን ህዝቡን ሊያነቁት እና ሊያደራጁት እንደሚገባ የፖለቲካ ተንታኞች ለአሻራ አብራርተዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply