የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት እና ብሩህ ማይንድስ ኮንሰልት በጋራ ለመስራት ተስማሙ

ዕረቡ ሐምሌ 6 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያን ኢንተርፕራይዝ ልማት እና የኢንተርፕራይዝ አማካሪ ድርጅት የሆነው ብሩህ ማይንድስ በዘርፉ ጥናቶች ላይ በጋራ ለመስራት ሥምነት ተፈራርመዋል።

ሥምምነቱ የተፈረመው ሦስተኛው የብሩህ ማይንድስ ወርሃዊ ልዩ ምልከታ የውይይት መድረክ ላይ ሲሆን፤ ሥምምነቱን ከብሩህ ማይንድስ ጋር የተፈራረሙት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ብሩህ ወልዴ ሥምምነቱ በሥራ ፈጠራና ኢንተርፕራይዞችን ለማጠናከር ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል።

አማካሪ ድርጅቶች ጋር አብሮ መስራት የኢንተርፕራይዞች መጎልበት ጉልህ ሚና እንዳለውም ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ብዙ ሀብት ቢኖራትም ያላትን ሀብት በአግባቡ እየተጠቀመች አለመሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልጸዋል።

ብሩህ ማይንድስ ኮንሰልት በየወሩ የሚያካሂደው የልዩ ምልከታ አዘጋጅ ለማ ወርቅ ደክሲሶ ሥምምነቱ በዘርፉ ጥናቶችን ለማድግና የኢንተርፕራይ ስልጠና ለመስጠት ያለመ መሆኑን አስረድተዋል።

የብሩህ ማይንድስ ወርሃዊ የውይይት መድረክ “የተቋማዊ አደረጃጀትና የቅንጅታዊ አሰራር ክፍተቶችና መፍትሔዎቻቸው የኢንተርፕርነርሽፕ ዘርፍ ልማት ማጎልበት በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ የዘርፉ ባለሙያዎችና የመንግሥት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በትናንትናው ዕለት ተካሂዷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply