የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በወሰን ማስከበር እና በካሳ ጥያቄዎች የተነሳ የጥገና ስራዎችን እንዳይከዉን ፈተና ሆኖብኛል አለ፡፡ከወሰን ማስከበር ጋር ተያይዞ በሚነሳው የካሳ ጥያቄ የኃይል ማስ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/c9CTPD4pbVzDxEWv9FSERYlWdY5SAn37V6CA0qTSrKeaUKUr8pc229DVujjZyG-EKXPHyAIysaL-0InsczZJfNUo2XwG98QdZZZ6RPU3MhVcsMcr33Npi075IrxdWn0l1yeB9NBt-HyzPPckiORFPk2lhRSLN4oWkmKer60kVkQ0rDSmlnSI0k9YHrAI0wIpgc_05GPT7AfeMhZ7b0RIopxR6CZNyK4_ZAbn9UExYJS-FMAuktSMqHtEkCq-QtsTF0aZp0ISDRJ4V6JND5VQg-Vlsaio-iVVhUaKSo45kiSIBtLWp-4Gx822-07W_G9_don3vggEi-7M5qnxQYm8Vg.jpg

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በወሰን ማስከበር እና በካሳ ጥያቄዎች የተነሳ የጥገና ስራዎችን እንዳይከዉን ፈተና ሆኖብኛል አለ፡፡

ከወሰን ማስከበር ጋር ተያይዞ በሚነሳው የካሳ ጥያቄ የኃይል ማስተላለፍ እና የኦፕሬሽን ጥገና ስራዎች በወቅቱ እንዳይከወኑ ፈተና ሆኖብኛል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል አስታዉቋል።

የደቡብ ምዕራብ ሪጂን ጨምሮ ከጂማ ዞን እስከ ጋምቤላ በተዘረጉ የማስተላለፊያ መስመሮች ላይ የካሳ ጥያቄዎች እየተነሱ በመሆኑ የፍተሻና የጥገና ሥራ ለማከናወን ፈተና እየሆነ መምጣቱን ገልጿል።

የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ሲሳይ እንዳሉት “የማስተላለፊያ መስመሮች በሚያልፉባቸው አካባቢዎች የሚቀርቡት የካሳ ይገባኛል ጥያቄዎች የኦፕሬሽንና ጥገና ሥራዎች በወቅቱ እንዳይከናወኑ እያደረጉ ይገኛሉ” ብለዋል።

በካሳ ጥያቄ የተነሳ ኃይል የማስተላለፍ ሥራ እየተስተጓጎለ እንደሆነና በቅርቡም የጊቤ 2 – ሰኮሩ መስመር ለአራት ቀናት ኃይል ማስተላለፍ ተቋርጦ ቆይቷል።

በተመሳሳይ ከመቱ – በደሌ እና መቱ -ጋምቤላ በተዘረጉ መስመሮች ላይ እየተፈፀመ ያለው ተደጋጋሚ ስርቆት መፍትሄ ባለማግኘቱ በኦፕሬሽን ሥራው ላይ ስጋት መደቀኑን ሰምተናል።

በልኡል ወልዴ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 02 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply