የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ደጀን ደብረ ማርቆስ የከፍተኛ መስመር ዝርጋታ ሰራተኞች በምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሰብሰቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል ታህሳስ 14 ቀን…

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ደጀን ደብረ ማርቆስ የከፍተኛ መስመር ዝርጋታ ሰራተኞች በምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሰብሰቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል ታህሳስ 14 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የማይተካ ህይወታቸውን ሰጥተው አሸባሪውን ቡድን በመደምሰስ እኛ በሰላም እንድንኖር እያደረጉ የሚገኙ የፀጥታ አካላትን ሰብል መሰብሰብና ቤተሰቦቻቸውን መንከባከብ ከኛ የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን በማመን የአንድ ቀን ስራችንን ዘግተን በደጀን ወረዳ ቦረቦር ቀበሌ በመገኘት የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብሰብላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሰራተኛ የሆኑት አቶ ዋለ ታምር እንደተናገሩት የሀገርን ሰላም ለማስከበር የማይተካ ህይወቱን ለኢትዮጵያ እየሰጠ ያለውን የፀጥታ አካላት ሰብልን ከመሰብሰብ ባለፈ የልማት ስራችንን ሳናቋርጥ ሌት ከቀን እየሰራን ነው ብለዋል። በህልውና ዘመቻው ግንባር የተሰለፉ የፀጥታ አካላትን ሰብል የመሰብሰብና የፈረሰ ቤታቸውን የመጠገን ተግባራትን አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል ያሉት አቶ ዋለ ወጣቱ ሀገር የገጠማትን ችግር ለመፍታትና ሉዓላዊነቷን በማስጠበቅ ማንነቱን ለማስከበር መከላከያና ልዩ ኃይልን በመቀላቀል የቀደመ የኢትዮጵያን አንድነት የማምጣት ግዴታ አለበት ብለዋል። በህልውና ዘመቻው የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር ግንባር የዘመቱ የሚሊሻ አባላትን ሰብል በመሰብሰብ የኋላ ደጀንነቴን በተግባር እያስመሰከርኩ በመሆኑ ኩራት ተሰምቶኛል ያሉት ደግሞ አቶ አስናቀ ምህረት ናቸው። የዘማች ቤተሰብ የሆነችው ግለሰብ እንደገለፀችው ባለቤቴ አገር ከሌለ እኛም የለንም በሚል ሀሳብ የሀገርን ጥሪ ተቀብሎ አገር ለማስከበር ወደ ግንባር ቢዘምትም የመብራት ኃይል ሰራተኞች ሰብሉ ሳይባክን አጭደው በመሰብሰብ ባደረጉልኝ ድጋፍ ደስታ ተሰምቶኛል ብላለች፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ደጀን ደብረ ማርቆስ የከፍተኛ መስመር ዝርጋታ ስራ አስኪያጅ አቶ እንዳለ ላቀው በበኩላቸው አሁን ባለው ወቅት ልማትና የህልውና ዘመቻው የማይነጣጠሉ በመሆናቸው ከመብራት ልማት ስራችን ጎን ለጎን በህልውና ዘመቻው ግንባር ለተሰለፉ የሚሊሻ አባላትን ሰብል መሰብሰብ እንዳለብን በማመን ወደ ስራ ገብተን እየሰራን ባለነው ስራ በህልውና ዘመቻውም ከማህረሰቡ ጎን መሆናችንን ማረጋገጥ ችለናል ብለዋል። የደጀን ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply