የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ዉድመት ደርሶብኛል አለ፡፡የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጦርነቱ በነበረባቸዉ ክልሎች ዉስጥ የነበረ የኔትወርክ ሲስተሙ ላይ ከአን…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/tMeNoUwLgeVa8Dlxoq0TYNC4McCk4UVn4eBzdt14vpzZj2tjwzNwbmUVqyY4zIUyOm3KyfujZtKSPaXsAZ5Apy_0P1GofYkYHds0E9IVaTrljoD_0PeXAVQwarvOyy737kLI6kl6_Y5DUE3lMgd6rPYZ9p1Us1-Nc0iuj6v5EhTsA-4C1GDTE4dHiNwRR5cQvqLhHTKTdZGzm__d03So54U5sxteR5b08SLRSW3mbLFPkJTm0mnKVo3K4vZ9NFOL7YHTDYZLBO-PXDMmAR3izGA4xK8g9CRTGFGEqvNeaRnLyJnIZUJ1xrZhWdCyKz7DNLF6ur19H7EuHyRT_HGnmw.jpg

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ዉድመት ደርሶብኛል አለ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጦርነቱ በነበረባቸዉ ክልሎች ዉስጥ የነበረ የኔትወርክ ሲስተሙ ላይ ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ዉድመት ደርሶብኛል ብሏል፡፡

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መላኩ ታዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደ ገለጹት በአገልግሎት ተቋሙ ላይ በአማራ እና አፋር ክልሎችላይ ከፍተኛ የሚባል ዉድመት እንደደረሰበት ገልጸዋል፡፡

በአፋር ክልል 6 አገልግሎት መስጫ ማዕከላት፣ በአማራ ክልል በ5 ዲስትሪክት ዉስጥ ባሉ 30 የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት እና ደሴና ወልዲያ ባሉ ሁለት የአገልግሎቱ ጽህፈት ቤቶች ላይ ዉድመት እና ዝርፊያዉ መካሄዱን ነግረዉናል፡፡

ተቋሙ ከዚህ ዉጭ ባለፉት 6 ወራት ዉስጥ ከባድ ግዜን ማሳለፉን ገልጸዉ፣ በዚህም ሌላ ችግር የነበረዉ የኤሌክትሪክ መሰረት ልማት ግብዓት የሚዉል ጥሬ ዕቃ ከዉጭ የሚገባ በመሆኑ የዉጭ ምንዛሬ ዕጥረት መኖሩ እና በተለያዩ የመሰረተ ልማቶች ላይ ስርቆት መፈጸሙ ነዉ ተብሏል፡፡

በ 6 ወራት ግዜ ዉስጥ ብቻ ከመሰረተ ልማት ጋር በተያያዘ 131 የሚሆኑ ወንጀሎች እንደነበሩ የገለጹት ዳይሬክተሩ፣
በ21 ክሶች ላይ ፍርድ መሰጠቱንና ከ 6 ወር እስከ 9 ዓመት በሚደርስ ቅጣት መቀጣታቸዉን ተናግረዋል፡፡

ቀሪዎቹ ደግሞ በፍርድ ሂደት ላይ መሆናቸዉን ነግረዉናል፡፡

እስከዳር ግርማ
መጋቢት 08 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply