የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደንበኞች ከ95 በመቶ በላይ ደንበኞቹ ክፍያቸውን በኦንላይን እየከፈሉ ነው አለ፡፡የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/rC-BB6EdSIGmNcLgyci_GAkcOYMSriXbcrv_E_G533S5gnt3EXhVQDna93QgzYI36PLuPUd8tn9W7rY6JwG8xWVEcEdBqyCE6Scul_1tGKrYBuKQi_Bqoxo1OZLBEpztSgq6lRFkTqM0lM7RWrKkD7kzsCzF2XcQK6z0x6hZyRphxYsaLmivRMK4U0amrP47qhBNbLYf9-zdTDQQsjQ2TXcrH-2XTJ5g3gtZoEks2b1CfbGhdqGKWOdQK0kT_o3eDK4pdjDdGKZlg8lnpZ-NVw--9oknLWHXy5vihgm2hncr6bD3Srix7GEtiSljmoKuQJOGsyFPLeR0LpZgusPA9g.jpg

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደንበኞች ከ95 በመቶ በላይ ደንበኞቹ ክፍያቸውን በኦንላይን እየከፈሉ ነው አለ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ ለጠቢያችን እንዳሉት በስምት ወር የስራ አፈፃፀም ከ95 በመቶ በላይ ዜጎች በዲጂታል ታግዘው ወርሃዊ ፊጆታዎችን ከፍለዋል ብለዋል።

በዚህም ማህበረሰቡ በፊት ለእንዲህ አይነት አገልግሎት ያባክን የነበረውን ጊዜ ከሞላ ጎደል ማስቀረት ችሏል ነው ያሉት።

አገልግሎቱ ከዚህ በለፈም ከነፃ የስልክ ጥሪ ጋር በተያያዘ ማዕከሉ በቀን 40 የስልክ ጥሪ ብቻ መቀበል የሚችል ሲሆን በይበልጥ ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለመሆ አሁን ላይ በቀን ከ200 በላይ ጥሪ መቀበል የሚችል መሰረተ ልማት መዘርጋቱን ነግረውናል።

ይህ ስረዓትERP ወይንም ኢንተርፕራይዚ ሪሶርስ ፕላኒንግ የሚባል ስርዓት ነው ተብሏል።

ማንኛውንም አገልግሎት ፈላጊ ማህበረሰብ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያስችል ነው ብለዋል።

በመጨረሻም ይህ የተዘረጋው ስረዓት በ905 ነፃ የስልክ መስመር ላይ ለመሳለቅ የሚደውሉትንና አገልግሎት ፈልገው የሚደውሉት ሰዎች መለየት የሚያስችል ነው ተብሏል።

በልዑል ወልዴ

ሚያዝያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply