የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ አገልግሎት በነገው እለት ሀይል ቢቋረጥ የ24 ሰዓት የጥገና አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁ አለ፡፡በነገው እለት የሚከበረውን የኢድ አል ፈጥር በዓልን አስመልክ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/MsbYDwvpia1T1Fmy28xru1CljIHySld0-7uY26UkXRADzxOH6lDJK4IeSQR8-iJywHOY0jzLzqdor-QFkB1mGKStxw59ucchqpC4FJxq_27i7hTlJ3K9ZQFs4i-FR5Ciyu3KEGChA1GygdmVpktUSbaj3Mj1ciJznJdX_dqPqhSGI6gthPL4tYtYCdbTZR9WeyaAHP0ze0MalbkJTkCOkWLRPZJ5nPp35gl5Qrl1rcH8EDZH_g5eweYcT6pOAqY25FNJk8VC4TKbTS2L89QBKggD3cYP9MSgn5psPTRAO1NaNCjC_naasqOqk7mEXOm7HFmZ_Rb3ti_-edlNIpnCOw.jpg

የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ አገልግሎት በነገው እለት ሀይል ቢቋረጥ የ24 ሰዓት የጥገና አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁ አለ፡፡

በነገው እለት የሚከበረውን የኢድ አል ፈጥር በዓልን አስመልክቶ በመላው የሀገራችን ክፍል የመብራት መቆራረጥ እንዳይከሰት በቂ ዚግጂ ማድረጉንም አገልግሎቱ አስታወቋል።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮርፖሬት ኮምንኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ ለጣቢያችን እንዳሉት የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዳይቋረጥ እንዲሁም ብልሽት ሲያጋጥም ፈጣኝ ምላሽ የሚሰጥ ቡድን መዘጋጀቱን ተናግረዋል ።

በበዓላት ወቅት ከመቼውም ጊዜ ይልቅ የኤሌክትሪክ የሃይል ፍላጎት የሚጨምር በመሆኑ በነገው እለት የኢድ በዓል ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በሙሉ አቅማችን ዝግጅት አድርገናል ብለዋል።

የድህረ ክፍያ ወይንም ካርድ እያስሞሉ ኃይል የሚጠቀሙ ደንበኞች ማስሞላት ይኖርባቸዋል ተብሏል።

የትም ቦታ ከመብራት ሃይል ጋር ተያይዞ ማንኛውም ቅሬታ ወይንም ችግር ሲኖር ማህበረሰቡ በ905 ላይ ወይንም 904 ነፃ የስልክ መስመር በመደወል ማንኛውም አገልግሎት ማግኘት ይችላል ተብሏል ።

በመጨረሻም ከዚህ በፊት በበዓል ወቅት በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ጉዳት ለማድረስ ወይንም በሰላም እንዳይከበር ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ በመኖራቸው ማህበረሰቡ ፣ፖሊስ አከባቢው በንቃት እንዲጠበቅ ሲሉ አሳስበዋል ።

ልዑል ወልዴ
ሚያዝያ 01 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply