የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በታላቅ የነጃሺ መስጅድ ላይ በደረሰው ጥቃት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 28 ቀን 2013 ዓ.ም         አዲ…

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በታላቅ የነጃሺ መስጅድ ላይ በደረሰው ጥቃት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 28 ቀን 2013 ዓ.ም አዲ…

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በታላቅ የነጃሺ መስጅድ ላይ በደረሰው ጥቃት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 28 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በታላቁ የነጃሺ ታሪካዊ መካነ ቅርስ መስጅድ ላይ የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። ምክር ቤቱ የዓለም ቅርስ በሆነው የነጃሺ ታሪካዊ መስጅድና የቀብር ቦታ ላይ በከባድ ጦር መሳሪያ በደረሰ ጥቃት በቅርሱ መስጅድ ላይ ጉዳት ደርሷል ብሏል። እንዲሁም የአገልግሎቶ መስጫ ተቋማት እና የመገልገያ ቁሳቁሶች ለዝርፊያ መጋለጣቸውንም ገልጿል፡፡ የታላቁ ንጉስ ነጃሺ እና የነብዩ መሐመድ (ሰዐወ) ባልደረቦች መቃብር እና በስሙ የተሰየሙ በዓለም የሚገኙ ቀደምት መስጂዶች አንዱ የሆነው ታሪካዊ ቦታ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን የመላው ዓለም ቅርስ ነውም ብሏል ምክር ቤቱ። መንግስት እና ህብረተሰቡ በመቀናጀት ይህን የወንጀል ድርጊት የፈጸሙ አካላትን በአፋጣኝ ለህግ እንዲያቀርቡም ጠይቋል ምክር ቤቱ፡፡ በዚህ ታላቅ ታሪካዊ ቅርስ እና መስጅድ ላይ በደረሰው ጉዳት የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ብቻ ሳይሆን የመላው ዓለም ሙስሊሞች ልብ ተሰብሯል ብሏል። ምክር ቤቱ ይህንን ፍፁም ፀያፍና አሳፋሪ የወንጀል ድርጊት በጽኑ እንደሚያወግዝም አስታውቋል።መንግስት እና ህብረተሰቡ በመቀናጀት ይህን አስነዋሪ ድርጊት የፈፀሙ አካላትን በአፋጣኝ ለፍትህ እንዲቀርቡም ጥሪ አቅርቧል። ከዚህ ጋር በተያያዘም ይህንን የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ትክክለኛውን መረጃ እና ማብራሪያ እንዲሰጥ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጥያቄ ማቅረቡንም ነው ያስታወቀው። እንዲሁም ቅርሱ የደረሰበትን ትክክለኛ ጉዳት እና የጉዳቱን መጠን የሚያጣራ ቡድን ከሚመለከታቸው የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣንና የምክር ቤቱ ባለሙያዎች ቡድን ወደ ቦታው ተልኮ ቡድኑ ሪፖርቱን በአጭር ጊዜ እንዲያቀርብ እየሰራ እንደሚገኝ ነው የተገለፀው፡፡ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ጥቃት የደረሰበት መስጅድና ቅርስ የሚመለከታቸውን አካላት በማስተባበር በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠግኖ የቀድሞ አገልግሎቱን እንዲሰጥ እንደሚያደርግና ለዚህም ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጿል ያለው FBC ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply