የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የጠቅላላ ጉባዔ እና የስራ አስፈጻሚ አባላትን መርጧል። ጠቅላላ ጉባዔው ሸኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋን በፕሬዝዳንትነት፣ ሸኽ አብዱልከሪም ሸኽ በድረዲ…

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የጠቅላላ ጉባዔ እና የስራ አስፈጻሚ አባላትን መርጧል።

ጠቅላላ ጉባዔው ሸኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋን በፕሬዝዳንትነት፣ ሸኽ አብዱልከሪም ሸኽ በድረዲን እና አብዱልዐዚዝ አብዱልወሌን በምክትል ፕሬዝዳንትነት እንዲሁም ሸኽ ሀሚድ ሙሳን በዋና ፀሐፊነት ሰይሟል።

ሚያዚያ 23 ቀን 2011 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተቋማዊ ለውጥና አንድነት አገር አቀፍ ጉባዔ የተመረጠው ኮሚቴ በስድስት ወራት ውስጥ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጎ አመራሮችን እንዲያስመርጥ ኅላፊነት ቢሰጠውም ኅላፊነቱን ሳይወጣ ለሶስት ዓመት ከስድስት ወር ቆይቷል።

በወቅቱ የተመረጠው ኮሚቴ ኅላፊነቱን ባለመወጣቱ ወደ መደበኛው ጉባዔ እንዲመጣ ዛሬ ለሁለተኛ ዙር አገር አቀፍ ጉባኤ ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ ተወካዮች በተገኙበት ተካሂዷል።

በጉባኤው ላይ በድምፅ ይሳተፋሉ ተብለው ከሚጠበቁት 300 ተሳታፊዎች መካከል 261ዱ ተገኝተዋል።

ሚያዚያ 23 ቀን 2011 ዓ.ም በተካሄደው ጉባኤ ከተሳተፉት መካከል 39ኙ በሞት፣ በህመም፣ ከሀጂ ጉዞ ባለመመለስና በልዩ ልዩ ምክንያቶች በዛሬው ጉባኤ አለመገኘታቸውም ታውቋል።

ጉባዔውን አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት የኅይማኖት አባቶች ስለምርጫው ሂደቱ ማብራሪያና የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል።

በጉባዔው ምርጫ ከመካሄዱ ቀደም ብሎ የምርጫ መስፈርቶች ለጉባዔው በንባብ ቀርበዋል።

በዛሬው ጉባዔ መጂሊሱን ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት የሚመሩ አመራሮች ምርጫ ተካሂዶ የሚከተሉት 14 ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን ተመርጠዋል።

ሸኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ
ሸኽ አብዱልከሪም ሸኽ በድረዲን
ሸኽ አልመርዲ ዐብዱላሂ
ሸኽ ሀሚድ ሙሳን
ሸኽ እድሪስ ዓሊይ ሁሴን
ሸኽ አብዱልዐዚዝ አብዱልወሌ
ሸኽ መሀመድ አህመድ ያሲን
ሸኽ አሚን ኢብሮ
ኢንጂኔር አንዋር ሙስጠፋ
10. ሸኽ አብዱልሃሚድ አህመድ
11. ሀጂ ሙስጠፋ ናስር
12. ሸኽ ዛኪር ኢብራሂም
13. ሸኽ ሁሴን ሀሰን
14. ሸኽ መሀመድ አሚን ሰይድ
ከስራ አስፈጻሚ አባላቱ መካከልም ሸኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋን በፕሬዝዳንትነት፣ ሸኽ አብዱልከሪም ሸኽ በድረዲን እና አብዱልዐዚዝ አብዱልወሌን በምክትል ፕሬዝዳንትነት እንዲሁም ሸኽ ሀሚድ ሙሳን በዋና ፀሐፊነት ሰይሟል።

በምርጫው ተሳታፊ የጠቅላላ ጉባዔ አባላት ስም ዝርዝር

ሸኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ
ሸኽ አብዱልዐዚዝ አብዱልወሌ
ሸኽ አልመርዲ አብዱላሂ
ሸኽ ሐሚድ ሙሳ
ሸኽ እድሪስ ዓሊይ ሁሴን
ሸኽ መሀመድ አህመድ ያሲን
ሸኽ አሚን ኢብሮ
ኢንጂኔር አንዋር ሙስጠፋ
9. አብዱልከሪም ሸኽ በድረዲን
10. ሸኽ አብዱልሃሚድ አህመድ
11. ሐጂ ሙስጠፋ ናስር
12. ሸኽ ዛኪር ኢብራሂም
13. ሸኽ ሁሴን ሀሰን
14. ሸኽ መሃመድ አሚን ሰይድ ዐያሽ
15. ሸኽ ጣሃ መሃመድ ሐሩን
16. ዑስታዝ አብዱራህማን ሱልጣን
17. ሸክ መሃመድ ዑመር ፈታህ
18. ሸኽ ዐብዱልመናን ማህሙድ አደም
19. ሸክ መሃመድ ኢብራሂም ወርቁ
20. ሸክ ዐብዶልሃዲ አህመድ ቡርሃን
21. ዑስታዝ ሙሀመድ ሙስጠፋ ዑመር

22. ሸክ አህመድ መሀመድ ዓሊይ

23. ሸክ ጁነይድ ሃምዛ የሱፍ

24. ዶክተር መሀመድ ሁሴን መሀመድ

25. ሸክ ሀቢብ ሙስጠፋ ሀሰን

26. ሸክ መሀመድ ዓሊይ ኸድር

27. ዑስታዝ ጋሊ አባቦር አባ ጎማን

28. ዑስታዝ ዚያድ አልይ ሁሴን

29. ሸክ አልኻድር አህመድ ዛይድ

30. ሸክ ኑረዲን ደሊል አወል

ተመራጩ ፕሬዝዳንት ሸኽ ኢብራሂም ቱፋ ባስተላለፉት መልዕክት ምርጫው ከየትኛውም አካል ጣልቃገብነት በጸዳ አግባብ በነጻነት ታሪካዊ ምርጫ እንደሆነ ተናግረዋል።

ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ታላቅ ኅላፊነት የተሰጣቸው መሆኑን የገለጹት ሸኽ ኢብራሂም ቱፋ፤ በተለይም የህዝብ ሙስሊምን አንድነት በማስጠበቅ ረገድ በትኩረት እንደሚሰሩ አረጋገጠዋል።

ህዝበ ሙስሊሙም ከጎናቸው እንዲቆም እና በጸሎት እንዲያግዛቸውም ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሐምሌ 11 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply