የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ በአዲስ መልክ ተዋቀረ

የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ሙሉ ለሙሉ በአዲስ መልክ እንዲዋቀር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ትናንት ባደረገው ስብሰባ ውሳኔ አሳልፏል።

ኮሚቴው በአዲስ መልክ እንዲዋቀር መነሻ የሆነው ጥቅምት 19/2016 በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የፀደቀው የተሻሻለው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መተዳደርያ ደንብ ሲሆን በደንቡ አንቀፅ 46 (ቁጥር 2) ላይ ቋሚ ኮሚቴዎች የሚቋቋሙበት ሁኔታ ሲገልፅ “ከብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ በቀር የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል

የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይም ምክትል ሰብሳቢ ሆኖ መስራት ይችላል።
” ይላል። የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴን አወቃቀር እና አሠራር ገለልተኛ ለማድረግም አባላቱ ከሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ውጪ እንደሚሆኑ በደንቡ ላይ ተቀምጧል።

በዚህም መሠረት የተሻሻለው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ደንብ ለፊፋ ተልኮ እንዲፀድቅ በመደረጉ ብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ በአዲስ መልክ እንዲዋቀር የተወሰነ ሲሆን ከዚህ ቀደም በኢንተርናሽናል ዳኝነት ሲያገለግሉ የቆዩ ግለሰቦች በአመራርነት ተመርጠዋል።

በአዲሱ የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ የተመረጡት አባላት የሚከተሉት ናቸው:-
ዋና ሰብሳቢ – ሸዋንግዛው ተባባል

ምክትል ሰብሳቢ – ሊዲያ ታፈሠ
አባል – ለሚ ንጉሤ
አባል – ክንዴ ሙሴ
አባል – ክንፈ ይልማ

ጋዲሳ መገርሳ

ሚያዚያ 11ቀን 2016 ዓ.ም

ኤትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጲያዊያን

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply