የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በእነ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ ላይ አስተላልፋው የነበረውን እገዳ ማንሳቷን አስታወቀች።የፓትሪያርክ ጽህፈት ቤት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው ቤተክርስቲ…

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በእነ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ ላይ አስተላልፋው የነበረውን እገዳ ማንሳቷን አስታወቀች።

የፓትሪያርክ ጽህፈት ቤት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው ቤተክርስቲያኗ የኦሮሚያ ቤተክህነትን ለማቋቋም በሚል በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ በነበሩት ላይ እገዳ አስተላልፋ ነበር።

ይሁንና እነዚህ ሰዎች ከቤተክርስቲያኗ ጋር ባደረጉት የእርቅ ስራ በእነ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ ላይ አስተላልፋው የነበረውን እገዳ ማንሳቷን አስታውቃለች።

እገዳው ተላልፎባቸው የነበሩት ሰዎች በቤተክርስቲያኗ መዋቅር ውስጥ ሆነው ሥራ እንዲሰሩም ውሳኔ ተላልፏል ተብሏል።

በመሆኑም እነቀሲስ በላይ በእርቁ ላይ ዛሬ ከሰዓት መግለጫ ይሰጣሉ ተብሏል።

በሳሙኤል አባተ
ጥቅምት 19 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply