
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መንግሥት የሚጠበቅበትን አስካላከናወነ ድረስ የፀጥታ እና ደኅነት የጋራ ግብረ ኃይል ያስተላለፈውን የሰልፍ ክልከላ እንደማትቀበለው አስታወቀች። ቤተክርስቲያኗ ይህን ያለችው ዛሬ ሐሙስ የካቲት 02/2015 ዓ.ም. ባለፉት ቀናት ስላጋጠሙ ጉዳዮች እና በመንግሥት በኩል የተላለፈውን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ በቅዱስ ሲኖዶሱ በኩል በተሰጠው መግለጫ ነው።
Source: Link to the Post