
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ውጪ ተሰጥቷል የተባለውን የጳጳሳት ሹመትን በተመለከተ የቤተክርስቲያኗ ፓትሪያርክ ጥሪ አቀረቡ። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ብፁዕ አቡነ አብርሃም እሁድ ከሰዓት በኋላ በቤተክርስቲያኗ የመገናኛ ብዙኃን ላይ ቀርበው ስለተከሰተው ሁኔታ ለመነጋገር በተለያዩ አካባቢዎች ላሉ ጳጳሳት፣ ለመንግሥት እና ለምዕመናን ጥሪ አቅርበዋል።
Source: Link to the Post