You are currently viewing የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንግስት በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቃት ብሎም  ለህገወጡ ቡድን እገዛ ከመስጠት እንዲታቀብ አሳሰበች። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ጥር 30 ቀን…

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንግስት በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቃት ብሎም ለህገወጡ ቡድን እገዛ ከመስጠት እንዲታቀብ አሳሰበች። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 30 ቀን…

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንግስት በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቃት ብሎም ለህገወጡ ቡድን እገዛ ከመስጠት እንዲታቀብ አሳሰበች። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 30 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ቤተ ክርስቲያን ህገ ወጥ አካላት እየፈፀሙት ላለው ድርጊት እገዛ ከመስጠት እንዲታቀብ ስትል መንግስትን ጠይቃለች። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥር 28/2015 ቤተክርስቲያኗን በተመለከተ በመንግስት የተሰጠውን መግለጫ ውድቅ አድርጋለች። በሻሸመኔ ከተማ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች የተፈጸመውን ሕገ ወጥ፤ አስነዋሪ እና ጭካኔ የተሞላበት የአደባባይ ግድያ እና የሕዝብ ፍጅት ያልጠቀሰና ሐዘኑን እንኳን መግለጽ ያልቻለበትና ያላወገዘን የመንግስት መግለጫ እንደማትቀበለው አስታውቃለች። የጥቃቱ ሁኔታ በመግለጫው እንኳ አለመጠቀሱ የመንግሥትን ግልጽ ሚና በቀላሉ ለመረዳት እንድንችል ያደርገናል ስትል አጋርታለች። “መንግሥት ሕገ ወጥ አካላትን ድጋፍ ከመስጠት እና የእነርሱ ልሳን ሆኖ በመቅረብ የቤተ ክርስቲያንን ክብር እና ልእልና ከሚያንኳስስ ሕገ ወጥ ድርጊት እንዲታቀብ እናሳስባለን” ስትልም አስጠንቅቃለች። “ሕገ ወጥ ስብስቦች እየፈጸሙ ላሉት ድርጊትም የሰጠውን ድጋፍ እና እገዛ በይፋ ቤተ ክርስቲያንን ይቅርታ በመጠየቅ ያቁም” ስትል ጠይቃለች።

Source: Link to the Post

Leave a Reply