የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተከስቶ የነበረው ችግር እንደተፈታ አስታወቀች::

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በውስጧ ተከስቶ የነበረው ችግር በቤተ ክርስቲያኗ ቀኖና እና ሥርዓት መሠረት እንደተፈታ አስታወቀች። በዚህም መሠረት የቤተክርስቲያኗን ሥርዓት እና ሕግ ጥሰዋል ተብለው በቅዱስ ሲኖዶሱ ተወግዘው ተለይተው የነበሩት አባቶችም ወደ ቤተክርስቲያኗ መመለሳቸው ተገልጿል። ሶስቱ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ሳዊሮስ፣ አቡነ ኤዎስጣቴዎስና አቡነ ዜና ማርቆስ ወደ ቀደመ ሃገረ ስብከታቸውና ማዕረጋቸው እንዲመለሱና ተሿሚዎቹ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመታቸው የጵጵስና ሹመታቸው ተሽሮ ወደነበሩበት የክህነት ማዕረግ እንዲመለሱ ተወስኗል። ከተሾሙት መካከል በቤተ ክርስቲያን ስርዓት ተመዝነው የሚያሟሉት በቅዱስ ሲኖዶሱ እንዲሾሙ ይደረጋል ተብሏል። …

Source: Link to the Post

Leave a Reply