የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የህክምና ማህበር አርቲስት ትግስት ግርማን አምባሳደር አድርጎ ሾመ።ማህበሩ ዛሬ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ በቀጣይ ለሚሰራቸዉ የበጎ አድራጎት እና የህክምና አገልግ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/Q0fNFJHUo9FY52wc8xw-m6tyZaZn73iehjTeCjZc6tKx_Z9pDeq6aVkjVtshdaE2qsPD_0NZsiFTvMIPRg6fk9O6HqkpEB-xDpy-uAORGq1_BrJcFjJE1ACkm-DKivP3j12dGVSqjY-bbf3P2rBq_QsqYMOfD4z-CWk4iDb_XN9T2UtuMMCx_TWF-h6_iADnwW6umowbBAbFN57kSSaY58z4i8KRJJoHwbMY1g-_SWkqnw5ga7VZ4P1k13PGcpFTh7Teq-RKqe49oL64GYnuXY5SrIvkdyh-mI5yGZ7md2tvwB_YugN1DFq89i_LMzzrPzQl5sVVKJcbjf6VZ749sw.jpg

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የህክምና ማህበር አርቲስት ትግስት ግርማን አምባሳደር አድርጎ ሾመ።

ማህበሩ ዛሬ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ በቀጣይ ለሚሰራቸዉ የበጎ አድራጎት እና የህክምና አገልግሎት አርቲስቷን የክብር አምባሳደር ማድረጉን አሳዉቋል።

ላለፉት ሶስት አመታት ከ35 በላይ የህክምና ጉዞዎችን በሀገሪቱ በማድረግ 26 ሺህ በላይ ሰዎችን የነፃ ህክምና ተጠቃሚ ማድረጉንም ገልፆል።

የኢትዪጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ማህበር የአዲስ አበባ ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም እንደገለፁት በቀጣዩቹ አመታት ግዙፍ ሪፈራል ሆስፒታል ለመገንባት እቅድ መያዙን አስታውቋል።

በ2013 ዓ/ ም በሀገረ አሜሪካን ምስረታዉን ያደረገዉ ማእከሉ 2500 በላይ በጎ ፍቃደኛ የህክምና ባለሙያዎች አባላት እንዳሉት ለማወቅ ተችሏል።

በቁምነገር አየለ

ሰኔ 20 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply