
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዛሬ በተሰማው ሕገ ወጥ “ሢመተ ጳጳሳት” ጉዳይ በሰጠችው መግለጫ ጉዳዩ ከቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ውጪ በሕገወጥነት የተከናወነ መሆኑን ማሳወቋ ይታወሳል።
በዚሁ ጉዳይ ላይ የመንግስት ኮሚንኬሽን አገልግሎት ሚንስትር ለገሰ ቱሉ ይህን ብለዋል።
”የአንድ ማህበረሰብ ወይም ሀገር ህዝቦች ህግና ስርዓት የሚመነጩት ከሰው ልጆች የዕድገት ደረጃ ፣ ንቃተ ህሊናና ማህበራዊ ስነ-ልቦና ፣የህዝቡ ፍላጎትና መሻት፣ እምነትና ቀኖና ነው።
ከምድራዊም ሆነ መንፈሳዊ ህግ፣ ስርአት፣ ትውፊትና ቀኖና ጋር የሚጋጭ የትኛውም ድርጊት መጨረሻው የሰመረ ሊሆን አይችልም።
ከክፍፍል ይልቅ አንድነትን፣ ከጥለቻ ይልቅ ፍቅርና ይቅርባይነትን መርህ አድርገን በሚንቀሳቀስበት ወቅት ከአንዱ የቤተክህነታችን ክፍል ዛሬ የሰማነው ድርጊት አሳዛኝ ዜና ነው።
አባቶች በትዕግሥት እና ሃይማኖታዊ ስርዓት ችግሩን ይፈታሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ጉዳዩን የተለያየ ፖለቲካዊ እና አካባቢያዊ ገፅታ መስጠትም ተገቢ አይደለም።
የእምነቱ ተከታይ አባቶች ሁኔታውን በስክነትና ቤተ-ክህነታዊ ስርዓት እንዲፈቱ ጉዳዩን ለነሱ መተው እጅጉን አስፈላጊ ነው።” ብለዋል።
Source: Link to the Post