የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰኞ እለት ተቋቁሟል የተባለውን ” መንበረ ጴጥሮስ ” አወገዘች፡፡አሁን በሕገወጥ ድርጊታቸው የቀጠሉትን ቡድኖች በፍርድ እንደምትጠይቅ አሳውቃለች፡፡…

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰኞ እለት ተቋቁሟል የተባለውን ” መንበረ ጴጥሮስ ” አወገዘች፡፡

አሁን በሕገወጥ ድርጊታቸው የቀጠሉትን ቡድኖች በፍርድ እንደምትጠይቅ አሳውቃለች፡፡
ባለፈው ዓመት በዚህ ወቅት ቤተክርስቲያን ” ሕገወጥ ” ባለችው መንገድ በጵጵስና ተሹመናል ካሉት እና በኃላም በእርቅ ወደቤተክርስቲያን ሳይመለሱ ከቀሩት መካከል አባ ገብረማርያም ነጋሳን ጨምሮ 4 አባቶች ትላንት በሰጡት መግለጫ ” የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ቤተክህነት መንበረ ጴጥሮስ ” አቋቁመናል ብለዋል።

ይህ በ2015 ዓ/ም ተቋቁሟል ላሉት የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መንበር መሰየም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቋሚና ጊዜያዊ ፕሮጀክት መምሪያ ኃላፊ መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ወ/ኢየሱስ ሰይፉ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህ መግለጫ ፤ ” ግለሰቦቹ በሌላቸው ክህነት ነው መግለጫ እየሰጡ ያሉት ” ብለዋል።

እነዚህን አካላት ያደረጉት ከቀኖና ውጭ ስለሆነ ዛሬም ቤተክርስቲያን አጥብቃ ታወግዛለች ሲሉ ተናግረዋል።

” ቤተክርስቲያን በሕግ በፍርድ ቤት ትጠይቃችለች ፤ በፍትህ መንፈሳዊ ከዚህ ቀደም እንዳወገዘችው አሁንም ህጌ፣ ስርዓቴ፣ ልብሴ ፣ ዶግማዬ ይከበር ትላለች ” ሲሉ አክለዋል።

” ከዚህ ቀደም በፍ/ቤት ከቤተክርስቲያን እውቅና ውጭ የትም እንዳይንቀሳቀሱ ፣ አገልግሎት እንዳይሰጡ ታግደው ነበር ያንን ተላልፈዋል ከዚህ በኃላ በፍርድ እንጠይቃቸዋለን፤ የለበሱት ልብስም የቤተክርስቲያን ስለሆነ እናስወልቃቸዋለን፤ ህገወጥ ናቸው ” ብለዋል።

” ከዚህ ባለፈ ይህ የሕገወጥ የሹመት እንቅስቃሴ ጉዳይ ከኦሮሚያ ወገን የተነሱትን ብቻ ሳይሆን ከትግራይ ወገን የተነሱትንም የሚመለከት ነው ” ያሉ ሲሆን ሲመቱ ትክክለኛ አይደለም ቅዱስ ሲኖዶስም አይቀበለውም ብለዋል።

በሌላ ዜና

“የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስትያን መንበረ ጴጥሮስ” ሲሉ የሰየሙትን ሲኖዶስ ማቋቋማቸውን ይፋ ካደረጉ የሃይማኖት አባቶች መካከል ሦስቱ ትላንት፤ ማክሰኞ መታሠራቸውን የእንቅስቃሴው አስተባባሪዎች ገልፀዋል።

አቡኖቹ የታሠሩት መግለጫውን ከሰጡ በኋላ ሸገር ከተማ አስተዳደር በሚገኘው ቢሯቸው ውስጥ እንዳሉ መሆኑን ከ“መንበር” ምሥረታው አስተባባሪዎች አንዱ መሆናቸውን ለቪኦኤ የተናገሩት ዲያቆን አክሊሉ ዓለሙ ገልፀዋል።

ስለሁኔታው ከሸገር ከተማ አስተዳደርና ከፖሊስ መምሪያው ምላሽ ለማግኘት ያደረኩት ጥረት አልተሳም ብሏል፡፡
ባለፈው ዓመት ተቀስቅሶ የነበረ ተመሳሳይ ውዝግብ ለሰው ህይወት መጥፋት ለንብረት ውድመት ምክንያት እንደነበረ የሚታወስ ነው፡፡
በኃላም ችግሮን ውይይት ተካሂዶ መቋጨቱ በወቅቱ ተዘግቦ ነበር።

ጥር 16 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply