You are currently viewing የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሕክምና ማኅበር “መጻጕዕን በመቄዶንያ” በሚል መሪ ቃል በመቄዶንያ የሕክምና አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    መጋቢት…

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሕክምና ማኅበር “መጻጕዕን በመቄዶንያ” በሚል መሪ ቃል በመቄዶንያ የሕክምና አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት…

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሕክምና ማኅበር “መጻጕዕን በመቄዶንያ” በሚል መሪ ቃል በመቄዶንያ የሕክምና አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 5 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ “መጻጕዕን በመቄዶንያ” በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሕክምና ማኅበር በመቄዶንያ የአረጋውያንና አእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል የሕክምና አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል። በመቄዶንያ እየተሰጠ የሚገኘው የሕክምና አገልግሎት በአብዛኛው የሥነ አእምሮ ላይ ያተኮረ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በበጎ ፈቃደኝነት የሚሳተፉ ከተለያዩ ስፔሺያሊቲ የተውጣጣጡ ባለ ሙያዎችን ያቀፈ መሆኑም ተጠቁሟል። የሕክምና ማኅበሩ የኢትዮጵያ ተወካይ ሊቀ ጠበብት ዶክተር ዘለዓለም ይርጋ ከተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ጋር ባደረጉት የስልክ ቃለ ምልልስ እስካሁን ከ300 በላይ ሕሙማን የሥነ አእምሮ፣ የውስጥ ደዌ እና የሥነ ልቡና የምክር አገልግሎት ማግኘታቸውን ገልጸው የአማኑኤል ሆስፒታል ለዚህ አገልግሎት ለተመደቡ ባለሙያዎች የሰርቪስ አገልግሎት በመስጠት ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል። የሕክምናው አገልግሎት ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ሲሆን ከሕክምና አገልግሎት መስጠቱ ጎን ለጎን በመቄዶንያ የሚገኙትን የሕሙማን መረጃ የማደራጀት ሥራም እየተሠራ ይገኛል ነው ያሉት። መጻጕዕን በመቄዶንያ የተሰኘው ይህ አገልግሎት የመጀመሪያው ዙር መሆኑን የገለጹት ሊቀ ጠበብት ዶክተር ዘላለም በቀጣዮቹ ዓመታት እንደሚቀጥልና አገልግሎቱን በማስፋት የቀዶ ጥገና ሐኪሞችን በመጨመር በቦታው ላይ መለስተኛ ቀዶ ጥገና እንዲሰጥ መታቀዱን አክለዋል። ተሚማ እንዳጋራው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply