
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልሎች በሚገኙ አገረ ስብከቶች የሚመደቡ የዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳትን መምረጡን ይፋ አደረገ። የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 28/2015 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ ክፍተት ባለባቸው፣ በተደራቢነት ተይዘው ለቆዩ እና ችግር አጋጥሟል ለተባሉ አገረ ስብከቶች ዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳትን መርጧል።
Source: Link to the Post