የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያሏትን ጥያቄዎች በመያዝ በተወካዮቿ አማካኝነት ማቅረብ ትችላለች ሲል የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ።የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽ…

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያሏትን ጥያቄዎች በመያዝ በተወካዮቿ አማካኝነት ማቅረብ ትችላለች ሲል የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑንም አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያሏትን ጥያቄዎች በቀጣይ በአጀንዳ ማሰባሰቢያ ላይ ማቅርብ እንደምትችልና በሩ ክፍት መሆኑን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን መግለፁን ሰምተናል።

ከሰሟኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ባወጣችዉ መግለጫ ቤተ እምነቷ እየተቃጠለ፣ አገልጋይ ካህናትና ምዕመናን እየሞቱና እየተሰደዱባት ለሚገጥሟት ችግሮች መፍትሔ እንዳታበጅና በሀገራዊ ምክክር መድረኩ ምንም ዓይነት ተሳትፎ እንዳይኖራት መደረጉ ተገቢ አይደለም ማለቷ ይታወሳል።

በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸዉን የሰጡን የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሠ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ባለድርሻ አካል ብሎ ከለያቸዉ ግንባር ቀደም መካከል አንዱ የዕምነት ተቋማት መሆናቸዉን ይገልፃሉ።

የዕምነት ተቋማት ኮሚሽኑ እንደተቋቋመ የመጀመሪያዉ ግንኙነት ካደረገባቸዉ መካከል አንዱ መሆኑም ይነሳሉ።

በዚህም የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሞ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

የሀይማኖት ተቋማት በቀጣይ በሚደረገዉ የአጀንዳ አሰባሰብ ላይ በየተቋሟቻቸዉ አጀንዳዎቻቸዉን በተወካዮቻቸዉ ማቅረብ እንደሚችሉም ይገልፃሉ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንም እንደሌሎች የሀይማኖት ተቋማት ሁሉ በሁሉም ወረዳዎች ጀምሮ በተወካዮቻቸዉ በኩል ሲሳተፉ መቆየታቸዉን ቃል አቀባዩ አንስተዋል።

ቤተክርስቲያኒቱ በቀጣይ በሚደረገዉ የአጀንዳ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ላይ ያላትን ጥያቄ ይዛ በተወካዮቻቸዉ አማካኝነት መሳተፍ እንደምትችልም አመላክተዋል።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቤተክርስቲያኒቱ የሚቀርቡ አጀንዳዎችንም ለዉይይት የማቅረብ ስራ እንደሚሰራ ተገልፃል።

አቤል ደጀኔ
መጋቢት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply