የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ አዲስ ጠቅላይ ጸኃፊ መረጠ።

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ባደረገው መደበኛ ጉባኤ አባ ከተማ አስፋው የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ጠቅላይ ጸኃፊ አድርጋ መሾሟን አስታውቃለች።

የጠቅላይ ጽ/ቤት ሀላፊ ሆነው የተመረጡት አባ ከተማ አስፋው ላለፉት ስድስት አመታት የጠቅላይ ጽ/ቤት የሐዋርያዊ ሥራዎች ኃላፊ  እና ጠቅላይ ጸኃፊ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩትን አቡነ ሉቃስን በመተካት መሆኑን ቤተክርስቲያኗ የገለጸችው።

ጠቅላይ ጸሀፊ የነበሩት አቡነ ሉቃስ በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የእምድብር ሀገረስብከት ተተኪ ጳጳስ ሆነው መሾማቸው ቤተክርስቲያኗ አስታውቃለች።

አሁን የጠቅላይ ጽ/ቤት ሀላፊ ሆነው የተመረጡት አባ ከተማ አስፋው ብፁዕ አቡነ ሉቃስን የሚተኩ ሲሆን ከሰኔ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የጠቅላይ ጸኃፊ ሀላፊነት ስራቸውን ይጀምራሉ ስትል ቤተክርስቲያኗ አስታውቃለች።

አባ ከተማ አስፋው የነቀምት ሀገረስብከት ካህን ሲሆኑ በካቶሊክ ዩኒቨርስቲ ላለፉት 16 ዓመታት በተለያዩ ዘርፎች በኃላፊነት እያገለገሉ ይገኛሉ ተብሏል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

መጋቢት 19 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply