የኢትዮጵያ ዕዳ ከዓመት ዓመት በፍጥነት እያደገ መምጣቱ ተገለፀ! ስቶክሆልም :- ሐምሌ 18/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ የዓለም ባንክ መረጃ እንደሚያመለክተው ደር…

የኢትዮጵያ ዕዳ ከዓመት ዓመት በፍጥነት እያደገ መምጣቱ ተገለፀ! ስቶክሆልም :- ሐምሌ 18/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ የዓለም ባንክ መረጃ እንደሚያመለክተው ደርግ ከሥልጣን ሲወርድ የኢትዮጵያ ዕዳ 9 ቢሊዮን ዶላር ነበር። ነገር ግን በ2006 የፈረንጆቹ ዓመት ይህ ዕዳ ወርዶ 2.2 ቢሊዮን ወርዶ የነበረ ቢሆንም፣ ከዚያ በኋላ ግን የኢትዮጵያ ዕዳ ከዓመት ዓመት በቢሊዮን ዶላሮች ይጨምር ያዘ። የዓለም ባንክ በፈረንጆቹ 2020 ባወጣው መረጃ የአገሪቱ ዕዳ 30.36 ቢሊዮን ዶላር ነበረ። እነሆ ከሁለት ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያ ከአገር ውስጥና ከውጭ የወሰደችው ብድር 56.6 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል ይላል የገንዘብ ሚኒስቴር። የኢትዮጵያ ዕዳ ከአገሪቱ አጠቃላይ ምርት ግማሽ ያክል መሆኑን ተከትሎ ባሉ ወቅታዊ የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ሁኔታዎች ምክንያት አበዳሪዎች በኢትዮጵያ እና በሌሎች አገራት የብድር አከፋፈሉ ዙሪያ ውይይት ይዘዋል። ከኢትዮጵያ የውጭ አበዳሪዎች የአንበሳውን ድርሻ የምትይዘው ቻይና እንዲሁም ፈረንሳይ ናቸው ስብሰባውን የሚመሩት። የኢትዮጵያ አበዳሪዎች ዕዳ ስለማሸጋሸግ ውይይት ማድረግ የጀመሩት ባለፈው ዓመት ነበር። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ)፣ የዓለም ባንክ፣ ሌሎች የገንዘብ ተቋማት ቻይና እና ሌሎች አበዳሪዎች ኢትዮጵያ፣ ቻድ እና ዛምቢያ ላለባቸው ዕዳ አስተያየት እንዲያደርጉ በመወትወት ላይ ናቸው። የአይኤምኤፍ ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ዕዳ ኖሮባቸው ተጨማሪ ፈተና እየገጠማቸው ላሉ አገራት መፍትሔ መበጀት አለበት ሲሉ ለሮይተርስ ዜና ወኪል ተናግረዋል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply