የኢትዮጵያ ዘውዳዊ ጉባኤ በኢትዮጵያ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጄኖሳይድ የማጋለጥና ማስረጃዎችን ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ እና ተቋማት የማድረስ ሥራ ማከናወኑን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አ…

የኢትዮጵያ ዘውዳዊ ጉባኤ በኢትዮጵያ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጄኖሳይድ የማጋለጥና ማስረጃዎችን ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ እና ተቋማት የማድረስ ሥራ ማከናወኑን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አ…

የኢትዮጵያ ዘውዳዊ ጉባኤ በኢትዮጵያ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጄኖሳይድ የማጋለጥና ማስረጃዎችን ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ እና ተቋማት የማድረስ ሥራ ማከናወኑን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 10 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የኢትዮጵያ ዘውዳዊ ጉባኤ በዚህ አንድ ዓመት ውስጥ ከናወናቸው ሥራዎች መካከል በጉልህነት የሚጠቀሱ በሚል ዘርዝሮ አስታውቋል። እንደአብነትም የጠፋውንና የተደበቀውን ታሪካዊ ሕዝባዊና ጥንተ መንግሥታዊ ማንነታችንን በሥነ ልቡና ዳግም ሕያው የማድረግ የማስነሳት ንቅናቄ ፈጥረናል ብሏል። የታሪክ እና የፖለቲካ ምርምሮችን በማካሄድ ሐሰተኛ አስተሳሰቦችን የማጋለጥና ሐቅን የማስታወቅ ሥራ አከናውነናል፤ የማይታወቁን እውቀቶች በማጉላት ሕዝባዊ ንቃተ ሕሊናን የማሳደግ ሥራዎችን ስለማከናወኑም የገለፀው የኢትዮጵያ ዘውዳዊ ጉባኤ በሥነ ልቡናው ጦርነት ለፍትሕ፣ በተለያዩ የሚድያ አውታሮችና በማሕበራዊ ሚዲያ ለሕዝብ ድምጽ በመሆንና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ግንኙነት በመፍጠር በሕዝብ ላይ የሚደርስን በደል የማጋለጥ ሥራ ሠርተናል ሲልም አክሏል። ፀረ ሕዝብ የሆኑ ኃይላትን በግልጽ አውግዘን በሥነ ልቡና ታግለናቸዋልም ብሏል። በሕዝባችን ላይ የሚፈጸመውን ጄኖሳይድ የማጋለጥና ማስረጃዎችን ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ እና ተቋማት የማድረስ ሥራ ስለማከናወኑ ብሎም ታሪካዊ እና ፖለቲካዊ ዕውቀትን የሚገነቡ፣ እንዲሁም ንቃተ ሕሊናን የሚያዳብሩ፣ ምሑራዊ ጥናቶች ላይ የተመሰረቱና ብዛት ያላቸው መጣጥፎችን እና ሚኒ ዶኩሜንተሪ ቪድዮዎችን አዘጋጅተን ለሕዝብ ንባብና እይታ አቅርበናል ነው ያለው። በተጨማሪም በዋሺንግተን ዲሲ ስብሰባ በማድረግ ዓላማችንን ይፋ አድርገንና መክረን በሕዝብ ግንኙነት እና በዲፕሎማሲ ዘርፍ በተዘዋዋሪ ውጤታማ የሆነ እንቅስቃሴ አድርገናል፤ ለሕዝብ የሚውል የገንዘብ ድጋፍም አድርገናል ብሏል። የሻከረውን ለማለስለስ የሕዝባችንን ማሕበራዊ-ፖለቲካዊ ችግሮችን አስመልክቶ ገላጭና አቅጣጫ ሰጭ የሆኑን ትንተናዎችና እይታዎች እያቀረብን ለፍትሕ ሙግት አካሂደናል። ለሕዝብ ግብዓት ይሆኑ ዘንድ የተለያዩ ዕውቀቶችን ያዘሉና ለሕትመት የሚውሉ ሰነዶችንም እያዘጋጀን እንገኛለን። በመጨረሻም ጥንካሬአችን የሚመጣው ከፈጣሪአችን ይሁንታ እና ከሕዝባችን ድጋፍ በመሆኑ እንደ አምላክ ፈቃድና እንደናንተ ድጋፍና ፍላጎት በመጪዎቹ ጊዜያት ለሕዝብ የሚጠቅሙን ሥራዎች በይበልጥ አግዝፈን ለመሥራት እናቅዳለን፤የፈጣሪአችን እና የእናንተ ድጋፍ እንደማይለየን በጽኑው እናምናለን ብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply