የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን መርጃ ማዕከል በዓመት ለ1 ሺ 500 ህጻናነት አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አቅም ቢኖረውም፤አሁን አገልግሎት እየሰጠ ያለው የአቅሙን አንድ ሶስተኛ ብቻ መሆኑን ሰምተ…

የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን መርጃ ማዕከል በዓመት ለ1 ሺ 500 ህጻናነት አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አቅም ቢኖረውም፤አሁን አገልግሎት እየሰጠ ያለው የአቅሙን አንድ ሶስተኛ ብቻ መሆኑን ሰምተናል፡፡

የመርጃ ማእከሉ የህዝብ ግኑኝነት ክፍል አላፊ የሆኑት አቶ ናሆም ሳምሶን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፤ማእከሉ በአመት ለ1 ሺ 500 ህጻናት የልብ ቀዶ ጥገና ማድረግ ቢችልም አሁን ላይ ግን እየሰጠ ያለው ለ500 ህጻናት ብቻ ነው ብለዋል፡፡

ሃላፊው ለዚህም ችግር እንደ ምክንያት ,ያነሱት ለአንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት ሰጥተው የሚወገዱ አላቂ እቃዎች የሚገቡት ከውጪ በመሆኑ እና ማዕከሉ ለዚህ መግዣ የሚሆን ቋሚ ገቢ ባለመኖሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚህም ምክኒያት በርካታ ህጻናት ወረፋ በመጠበቅ ህይወታቸው እንደሚያልፍ ገልጸው፤በአሁኑ ሰዓትም ከ7 ሺ በላይ የሚሆኑ ህጻናት ወረፋ እየጠበቁ መሆናቸውን ነግረውናል፡፡

ስለዚህ በአንድ ብር የአንድ ህጻን ልጅን ህይውት ማዳን እንደሚቻል የተናገሩት አቶ ናሆም ሁሉም ማህበረሰብ ለመርጃ ማእከሉ በተዘጋጀ 6710 በአጭር የጽሁፍ መልእክት ok ብሎ በመላክ የበኩሉን እንዲወጣ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የመረጃ ማእከሉ በዛሬው እለት ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም የምታሰባስባቸውን ገቢዎች ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል በማበርከት ከምትታወቀው ጋዜጠኛ ህይወት ታደሰ፤ በማህበራዊ ሚዲያ ያሰባሰበችውን 1 ነጥብ 2 ሚልየን ብር ተረክቧል፡፡

ጋዜጠኛ ህይወት ታደሰ ባለፉት ሶስት አመታት ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ባሰባሰበችው 3 ሚሊዬን ብር የሰላሳ ህጻናትን ህይወት መታደግ መቻሏም ተገልጿል ፡፡

ከተቋቋመ ሶስት አስርት አመታትን ያስቆጠረው የልብ ህሙማን መርጃ ማእከሉ ላለፉት 20 አመታት 2 ሺ 700 ታካሚዎች ወደ ወጪ ልኮ እንዲታከሙ አድርጓል፡፡

የመርጃ ማእከሉ በኢትዮጵያ ከተገነባበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት አምስት አመታት በድምሩ 5 ሺ 500 ህጻናት የልብ ቀዶ ጥገና ህክምና እንደተደረገላቸው ከማእከሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በመሳይ ገ/ መድህን

ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply