የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ የሶስት ቀናት ብሄራዊ የፀሎት እና የንስሃ መርሃግብር ማዘጋጀቱን አስታወቀ
የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ ከጷጉሜ 3 እስከ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የሶስት ቀናት ብሄራዊ የፀሎት እና የንስሃ መርሃግብር ማዘጋጀቱን አስታዉቋል።
መርሐ ግብሩ ጥላቻ የራቀበት የፍቅር ብሩህ ተስፋ የሚታይበትን አዲስ አመት እንቀበል’ የሚል መርህ እንደሚኖረውም ተገልጿል፡፡
የፀሎት እና የንስሃ መርሐ ግብሩ ይቅር በመባባል የጋራ አካባቢ እና ሀገር መገንባት እንዲያስችል ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን የሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ፀሀፊ ሊቀትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ተናግረዋል።
መርሐ ግብሩ የሚከናወነው እንደየቤተእምነቱ አስተምሮ እና ስርዓት መሆኑም ተጠቅሷል፡፡
ጷጉሜ 3 በእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስር ባሉት ሁሉም መስኪዶች የፀሎት ስነ-ስርዓት የሚደረግ ይሆናል፡፡
ጷጉሜ 4 በኢትዮጵያ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት የፀሎት ስነ-ስርዓት የሚደረግ ይሆናል ተብሏል።
ጷጉሜ 5 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፣ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን፣ በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረት፣ በመካነየሱስ እንዲሁም በኢትዮጵያ ቃለህይወት ቤተክርስቲያን የፀሎት እና የትምህርት መርሐ ግብር እንደሚኖርም ተጠቁሟል፡፡
በተጨማሪም ጷጉሜ 5 ከሰዓት በኋላ በወዳጅነት አደባባይ የሁሉም ቤተ-እምነት አባቶች እንዲሁም አማኞች እና የመንግስት አመራሮች በተገኙበት የማጠቃለያ የፀሎት መርሐ ግብር ይኖራል ነዉ የተባለዉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዉያን!
ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video

Telegram
Ethio Fm 107.8
በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
Source: Link to the Post