የኢትዮጵያ የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በመተከል ዞን ማንነትን መሰረት ያደረገ የጅምላ ጭፍጨፋ መካሄዱን አረጋገጠ፡፡                አሻራ ሚዲያ…

የኢትዮጵያ የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በመተከል ዞን ማንነትን መሰረት ያደረገ የጅምላ ጭፍጨፋ መካሄዱን አረጋገጠ፡፡ አሻራ ሚዲያ…

የኢትዮጵያ የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በመተከል ዞን ማንነትን መሰረት ያደረገ የጅምላ ጭፍጨፋ መካሄዱን አረጋገጠ፡፡ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 16/04/13/ዓ.ም ባህር ዳር በመተከል ዞን ማንነትን መሰረት ያደረገ የጅምላ ጭፍጨፋ መካሄዱን የኢትዮጵያ የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ባካሄደው የጥናትና ቁጥጥር ስራ አረጋግጧል። ተቋሙ እንዳስታወቀው በመተከል ዞን እየደረሰ ባለው የዜጎች ጭፍጨፋ፣ የንብረት ውድመትና ከቤት መፈናቀል የክልሉ መንግስትና የጸጥታ መዋቅር ድርጊቱን መከላከልና ማስቆም ለምን እንዳልቻሉ ለመመርመርና ለማጥናት ሞክሯል። ጉዳዩን የሚመረምር የጥናትና ቁጥጥር ቡድን ወደ አካባቢው በመላክ ባደረገው ጥናትም በዞኑ ማንዱራ፣ ዳንጉር፣ ጉባ፣ ድባጤ፣ ቡለንና ወንበራ ወረዳዎች ማንነትን መሰረት ያደረገ የጅምላ ጭፍጨፋ የተካሄደ መሆኑን እንዳረጋገጠ አመልክቷል። በተፈጸመው የወንጀል ድርጊት የክልሉ መንግስት አስተዳደር አካላት፣ የፓርቲ አመራሮችና የጸጥታ መዋቅር አካላት እንደተሳተፉም ጠቁሟል። ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌዴራል መንግስት አካላት የነበራቸው ድጋፍና ክትትል ዝቅተኛ እንደነበር ገልጾ ጉዳዩን በቅርበት ሲከታተል የነበረው የኮማንድ ፖስት ከችግሩ ክብደትና ስፋት አንጻር የሰራው የጸጥታ ማስከበር ስራና በአጥፊዎች ላይ የወሰደው እርምጃ ደካማ እንደነበር የተቋሙ የጥናትና የቁጥጥር ቡድኑ ለይቷል። ተቋሙ የክልሉ የአስተዳደር አካላትና የጸጥታ መዋቅር በወንጀል ድርጊቱ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እጃቸው እንዳለበት እንደሚያምን ገልጿል። በመጨረሻም ተቋሙ በወንጀል ድርጊቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳታፊ የነበሩ አካላት በህግ እንዲጠየቁ፣ ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድና ለሕዝቡም ይፋ እንዲሆን ጠይቋል። ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply