የኢትዮጵያ የማስታወቂያ ሥራ ማህበር አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውን አካሄደ

ሐሙስ ታህሳስ 4 ቀን 2016(አዲስ ማለዳ)የኢትዮጵያ የማስታወቂያ ሥራ ማህበር አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት ታህሳስ 4 2016 የማህበሩ አባላት፣ በማስታወቂያ ዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች እና የመንግስት አካላት በተገኙበት አካሂዷል።

እንዲሁም አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የሥራ አስፈጻሚዎች ምርጫ ያካሄደ ሲሆን፤ የማስታወቂያ ስራውን ከማዘመን ጋር ተያይዞ የወጡ መመሪያዎች እና አዳዲስ አሰራሮች ላይም ውይይት ተደርጓል።

በተለይም አዲስ አበባን ውብ እና ጽዱ ለማድረግ በከተማዋ ውስጥ የሚሰቀሉ ማስታወቂያዎች ዲጂታል ይደረጉ መባሉን በተመለከተ፤ የተለያዩ ሀሳቦችና ቅሬታዎች ተነስተዋል።

የከተማ አስተዳደሩ የከተማውን ማስታወቂያ ለማዘመን የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ የማስታወቂያ ሥራ ማህበር እንደ ባለድርሻ አካል ምክረ ሀሳቦችን እና የመፍትሔ ሀሳቦችን አመልክቷል።

የኢትዮጵያ የማስታወቂያ ሥራ ማህበር በዘርፍ ተሰማርቶ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማስታወቂያ ሥራ ለመስራት ህጋዊ ፍቃድና እውቅና የተሰጠው ሲሆን፤ በአዲስ አበባ እና በመላው አገሪቱ የተለያዩ ደረጃቸውን የጠበቁ የማስታወቂያ ሥራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply