የኢትዮጵያ የሽግግር ፍትህ ከ29 ዓመታት በፊት ጀምሮ ያሉ በደሎችን ተጠያቂ ያደርጋል ተባለ፡፡

ለፍትህ ሚኒስቴር የቀረበውና እንዲፀድቅ የሚጠበቀው የሽግግር ፍትህ ሪቂቅ የሰሜኑ ጦርነት ላይ ብቻ የሚያተኩር አለመሆኑንም ጣብያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

የሽግግር ፍትህ አንዲት አገር ወይም አንድ ሕዝብ ከጨቋኝ ሥርዓት ወደ ተሻለ ለማለፍ ወይም ከግጭትና ቀውስ ለመሸጋገር፤ወይም በእርስበርስ ግጭት ምክንያት ከደረሱ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና የተለያዩ ጉዳቶች በኋላ ዘላቂ ሰላምና እርቅ በመፍጠር የአገርን የወደፊት እጣ ፈንታ ለማስተካከል የሚታለፍበት የፍትሕ ሂደት ስለመሆኑ ይነሳል፡፡

በመሆኑም በኢትዮጵያ የረቀቀውና በቅርቡ ይፀድቃል ተብሎ የሚጠበቀው የሽግግር ፍትህ ረቂቅ በኢትዮጵያ ህገ-መንግስቱ ከፀደቀበት ከ1987 ዓ.ም ግዜ አንስቶ የነበሩ ጉዳዮች ላይ ተጠያቂ ያደረጋል ተብሏል፡፡

በርካቶች የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ጨምሮ የሽግግር ፍትህ ረቂቅ የሰሜኑ ጦርነት ላይ ብቻ ያተኮረ ይመስላቸዋል የሚሉት ረቂቁን በማዘጋጀት የተሳተፉት ዶ/ር ማርሸት ታደሠ፣ ይሁን እንጂ አዲስ የረቀቀው የሽግር ፍትህ በኢትዮጵያ ከ29 ዓመታት በፊት የተፈፀሙ በደሎችን ጭምር ተጠያቂ የሚያደርግ ረቂቅ መሆኑን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ዶክተር ማርሸት ከዚህ በተጨማሪ የሽግግር ፍትህ ረቂቁ ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን በተለይም በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ /ህውሃት/ አካላት የሚነሳበትን የገለልተኝነትና በውጭ አካላት መሳተፍ አለባቸው የሚለው ቅሬታ በተመለከተ ሲያስረዱ፤
“የውጭ አካላት ማለትም የኤርትራ ሰራዊት በጦርነቱ መሳተፉ እውነት ነው ይላሉ፤ በኢትዮጵያ መሬት አስከተካሄደ ድረስም ተጠያቂ ማድረግ ይቻላል፤ ይሁን እንጂ ይህ የሚሆነው የኤርትራ መንግስት ፍቃደኛ ሲሆን ብቻ ነው” ሲሉ ይናገራሉ፡፡
በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትህ የሚመስሉ የተለያዩ ሙከራዎች መደረጋቸው የተገለፀ ሲሆን ብዙዎቹ መሠረታዊ ስህተት እንደነበረባቸው ይነሳል፡፡

ተቃውሞና ድጋፍ የሚቸረው የሽግግር ፍትህ ረቂቅ ከሰሜኑ ጦርነት በተጨማሪ በኢትዮጵያ ባለፉት 29 ዓመታት የተፈፀሙ በደሎችን ተጠያቂ ለማድረግ ረቂቅ ተዘጋጅቶ እንዲፀደቅ ለመንግስት ቀርቦ እየተጠበቀ ይገኛል፡፡

በአቤል ደጀኔ
የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply