
ኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከምታስገባባቸው ምርቶች መካከል ቡና ለረጅም ጊዜ ቀዳሚ በመሆን ቆይቷል። ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚሰበሰበው የኢትዮጵያ ቡና በጣዕሙ የተለየ በመሆኑ ለተፈላጊነቱ ከፍተኛ ሆኖ ቆይቷል። በተለያዩ ጊዜያት በአገር ውስጥ በሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች እና ዓለም አቀፋዊ ክስተቶች ሳቢያ የቡና ዋጋ ከፍና ዝቅ ሲል ቆይቷል። አሁን ደግሞ የፀጥታ ችግር እና ሌሎች ሁኔታዎች የቡና ገበያውን እየፈተኑት መሆናቸው ይነገራል።
Source: Link to the Post