የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት (ኢባትሎአድ) በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 1.45 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀኢባትሎአድ በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ…

https://cdn4.telesco.pe/file/Teg43qLO8RLSAErQI23ZrCWFsg-KJ7fhCNl_0-CLuZica_aP-EmrsVq-59KNg8HirgaYoBMuomjzN6wgbb6xzOpCL3CD1TFmDD2SOnBOi0N3TsoPnjiaLoMmt6EXISqNvs3Vxg-EkHgEAWRnb0F3PWaTa2eeuDmDb_e7m8myIlfo1b_3w93dC8wRRtEBV0yuWSPwmVLnpwof6odc7mvfPM2SvGgmRV1FZCtOG9vWmYVZjVo1qtsKKnKRS8T16GIoYAkTv5tBq2eYNs1CaOlq_aAAPL32_A97SQUmweUIiPOaD_nf7r4IE0TTcrw1CWWxokZf-95JansUjZH-TSYPjw.jpg

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት (ኢባትሎአድ) በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 1.45 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

ኢባትሎአድ በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በባሕር ትራንስፖርት፣ በጭነት ማስተላለፍና በወደብና ተርሚናል ዘርፍ ከሚሰጣቸው የተለያዩ አገልግሎቶች 9.71 ቢሊዮን ብር ገቢ በማግኘት ከታክስ በፊት 1.45 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሮባ መገርሳ ገለጹ፡፡

ኢባትሎአድ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት 1.3 ሚልዮን ገቢና ወጪ ጭነት ያስተናገደ ሲሆን፤ በባሕር ትራንስፖርት (በሺፒንግ) አገልግሎት የድርጅቱንና የኪራይ መርከቦችን በመጠቀም ከ827ሺ በላይ ቶን ዕቃ አጓጉዟል፡፡ በጭነት ማስተላለፍ አገልግሎት 29ሺ TEU ኮንቴይነር እና ከ600 በላይ ተሽከርካሪዎችን በመልቲሞዳል የትራንስፖርት ስርዓት ወደ ሀገር ውስጥ ደረቅ ወደቦችና የጉምሩክ ፈቃድ ያላቸው መጋዘኖች ያጓጓዘ ሲሆን፤ 311ሺ 375 ቶን ገቢ ጭነት እና 63ሺ 795 ቶን ወጪ ጭነት በዩኒሞዳል የትራንስፖርት ስርዓት ማስተላለፍ ችሏል፡፡

እንዲሁም በወደብና ተርሚናል አገልግሎት በሩብ ዓመቱ አጠቃላይ የገቢና ወጪ ኮንቴይነር ፍሰት (Container Throughput) 102ሺ 299 TEU ኮንቴይነሮች በደረቅ ወደቦች የተስተናገዱ ሲሆን፤ ለ11ሺ 222 ቶን ዕቃ የዝግ መጋዘን እና ለ12ሺ 575 TEU ኮንቴይነር የአንስታፊንግ/ስታፊንግ አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ድርጅቱ ከሚሰጣቸው የተለያዩ አገልግሎቶች 9.71 ቢሊዮን ብር ገቢ የሰበሰበ ሲሆን፤ ከታክስ በፊት 1.45 ቢሊዮን ብር ትርፍ በማግኘት ዕቅዱን ማሳካት መቻሉን ድርጅቱ የላከልን መረጃ ያመለክታል፡፡

ህዳር 10 ቀን፣2014 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

Source: Link to the Post

Leave a Reply