የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2016 የሐጅ ምዝገባ ቀናት መራዘሙን አሳውቋል።ምክር ቤቱ ዘንድሮ የምዝገባ ሂደቱን ከተለመደው ጊዜ ቀደም ብሎ ማስጀመሩ ይታወሳል።የሳዑዲ ሐ…

የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2016 የሐጅ ምዝገባ ቀናት መራዘሙን አሳውቋል።

ምክር ቤቱ ዘንድሮ የምዝገባ ሂደቱን ከተለመደው ጊዜ ቀደም ብሎ ማስጀመሩ ይታወሳል።

የሳዑዲ ሐጅ ሚኒስቴር ከወትሮ በተለየ መልኩ የአመዘጋገቡን ሂደት እና የምዝገባ ጊዜውን ቀደም ብሎ በማስጀመሩ ብቻ ሳይሆን ክፊያዎች የሚጠናቀቁበትን የጊዜ ገደብ ጭምር በመገደቡ የተነሳ ኢትዮጵያን ጨምሮ አብዛኛው የዓለም ሃገራት በተፈለገው ፍጥነት እና በተቀመጠው ቀነ ገደብ የሚፈለግባቸውን ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት እንዳልቻሉ ተገልጿል።

በዚህም የሐጅ ምዝገባው እንዲራዘም ምክር ቤቱ ጉዳዩ ከሚመለከተው የሳዑዲ ሐጅ ሚኒስቴር ጋር ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ተደርጓል።

በዛሬው እለት ይጠናቀቅ የነበረው የምዝገባ ሂደት የዓመቱ ኮታ እስኪሞላ ድረስ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሐጅ አብይ ኮሚቴ የምዝገባ ሂደቱ

እንደሚቀጥል በወሰነው ውሳኔ መሰረት ምዝገባው የሚቀጥል ይሆናል።
እስካሁን ድረስ ቀርበው ያልተመዘገቡ ሑጃጆች በቀረው ጊዜና ኮታ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

ጥር 25 ቀን 2016 በ27 ምዝገባ ጣቢያዎች የዘንድሮውን የሐጅ ምዝገባ የጀመረው ጠቅላይ ምክር ቤቱ የእቅዱን 80% ሀጃጆችን መመዝገቡን አሳውቋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply