
ጥቅማችን አልተከበረም ያሉ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ ለማድረግ እንደተዘጋጁ ሲገልጹ፣ የመምህራን ማኅበር ደግሞ ስለተጠራው አድማ የማውቀው ነገር የለም ብሏል። የጥሪው አስተባባሪ ነን ያሉ መምህራን ለቢቢሲ እንደተገጹት ያቀረብናቸው ጥያቄዎች ምላሽ እስከሚያገኙ ድረስ ከሰኞ ኅዳር 26/2014 በጀምሮ የዩኒቨርሲቲ መምህራን በሥራ ገበታቸው ላይ እንደማይገኙ የገለጹ ሲሆን፣ ይህንንም ለሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ግልጽ ድብዳቤ መጻፋቸውን አስታውቀዋል።
Source: Link to the Post