የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢኒስቲትዩት ደረጃዎችን የሚያዘጋጁ በቂ የሆኑ ባለሙያዎች የሉኝም አለ፡፡ደርጃዎች ሲዘጋጁ ብዙ አይነት አሰራዎች ስላሉት እና ብዙ ባለድርሻ አካላት የሚያሳትፍ በመሆኑ በበ…

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢኒስቲትዩት ደረጃዎችን የሚያዘጋጁ በቂ የሆኑ ባለሙያዎች የሉኝም አለ፡፡

ደርጃዎች ሲዘጋጁ ብዙ አይነት አሰራዎች ስላሉት እና ብዙ ባለድርሻ አካላት የሚያሳትፍ በመሆኑ በበቂ ሁኔታ እነዚህን አካላት አምጥቶ ስራውን ለምስራት እንደሚቸገር አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር መሰረት በቀለ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በዘርፉ ላይ የተጠኑ ጥናቶችን ሰብስቦ ወደሀገራችን አምጥቶ መስራት ሌላኛው እንቅፋት ነው ብለዋል።

እራሱን የቻለ የጥናት ክፍል በማቋቋም ችግሩን ለመቅረፍ እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

ከ3 መቶ 50 በላይ ደረጃዎች መኖራቸውን እና አብዛኞቹ የምግብ ደረጃዎች መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡
የምግብ ደረጃዎች የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ በፍቃደኝነትም በአስገዳጅም ደረጃዎችን በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል ፡፡

ከውሃ ጀምሮ ውተት ፣ስኳር ፣ጨው እና የጁስ ምርቶች አብዛኞቹ አስገዳጅ ደረጃዎች ናቸው ብለዋል፡፡
አብዛኞቹ ግን ደረጃውን እና የአሰራር ስራቱን ተከትለው ነው የሚሰሩት የሚለው ጥያቄ የሚፈጥር መሆኑን አንስተዋል፡፡

ሶስት አይነት የደረጃ አዘገጃጀት እንዳለ የነገሩን ዋና ዳይሬክተሯ አንደኛው ሌሎች አለማት የሚያወጡትን ደረጃ ቀጥታ መውሰድ፣ ሁለተኛው ከሌሎች የተወሰደውን ደረጃ ወደ ሀገራችን አምጥቶ ባለው ነባራዊ ሁኔታ ቀይሮ መውሰድ ሲሆን ሶስተኛው ደግሞ ሀገር በቀል የሆነ እና በሃገር ውስጥ ብቻ የሚመረቱ ምርቶች ላይ በራሱ ጥናት ተሰርቶ የሚወጡ ደረጃዎች መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

በሶስተኛው አዘገጃጅት ከሚወጡ ደረጃዎች መካከል የጤፍ ደረጃን እንደአብነት አንስተዋል፡፡

ደረጃውን ማዘጋጀት ብቻ ሳይሆን እነዚህ ደረጃዎች በትክክል መተግበራቸውን ለማየት እና በተለይ ከምልክት ጋር ተያይዞ ያሉ ስራዎችን በትኩረት እየሰሩ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡

በሐመረ ፍሬው

ሰኔ 03 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply