የኢትዮጵያ የጥናት እና ምርምር ዘርፍ በዳዴ እየዳኽ ያለ ነው ተባለ።በተጠናቀቀዉ የፈረንጆች 2021 በዘርፉ በወጣ የግሎባል ኢንዴክስ ደረጃ መሠረት ከ131 ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ 127ኛ ደ…

የኢትዮጵያ የጥናት እና ምርምር ዘርፍ በዳዴ እየዳኽ ያለ ነው ተባለ።

በተጠናቀቀዉ የፈረንጆች 2021 በዘርፉ በወጣ የግሎባል ኢንዴክስ ደረጃ መሠረት ከ131 ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ 127ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧ የሀገሪቱ በጥናትና ምርምር ገና በዳዴ ላይ ያለ ዘርፍ መሆኑን ያመላክታል ተብሏል።

ይህ የተገለጸው በዛሬው ኢንተር ሌግዠሪ አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ባለው አገር አቀፍ ምርምር ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ላይ ነው።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የፖሊሲና ስትራቴጂ እቅድ ዳይሬክተር አቶ ደስታ አበራ እንዳሉት ከ2007 እስከ 2012 ዓ.ም ድረስ በጀት ተመድቦላቸው ሲሰሩ ከነበሩ ጥናቶች ውስጥ 60 የሚሆኑት የተጠናቀቁና በቅርቡንም የሚጠናቀቁ እንዳሉ ተገልጿል።

ምርምሮችም 24ቱ በግብርና፣ 18 የሚሆኑት ደግሞ በኢንዱስትሪ ፣ 6 ቱ በአይሲቲ እና በሌሎችም ዘርፎች የተከናወኑ መሆናቸው ተገልጿል።

የበጀት እና የምርምር እንዲሁም በዘርፍ ብቁ የሆነ የሰው ሀይል እጥረት የሀገሪቱን የጥናትና ምርምር ዘርፍ በእጅጉ እየፈተኑ የሚገኙ ማነቆዎች መሆናቸው ተነግሯል።

በሙሉቀን አሰፋ
ታህሳስ 27 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply