የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ህጋዊ ሰውነት ባለመያዜ ስራዬን በአግባቡ ለመስራት ተቸግሪያለው አለ

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ደስታ ዲንቃ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ፣ ምክር ቤቱ  ህጋዊ የሆነ ሰውነት ባለመያዙ እንደፈለገ እየተንቀሳቀሰ መስራት አልቻለም ብለዋል ።

በዚህም  በጀት እየተመደበላቸው እንዳለሆነ የሚናገሩት አቶ ደስታ የተለያዩ ስራዎችን በምንሰራበት ሰዓት ህጋዊ ሰውነታችሁን አሳዩን የሚል ጥያቄ በሚቀርብበት ሰዓት የምናቀርበው ሰነድ ባለመያዛችን ተቸግረናል ሲሉ ገልጸዋል።

መጋቢት 5 ቀን 2011 ዓ/ም በቃል ኪዳኑ ሰነድ አማካኝነት የጋራ ምክር ቤቱ እንደተቋቋመ የሚያነሱት ዋና ሰብሳቢው  በሰነዱም መሰረት እስካሁን ብዙ ስራዎች እንደሰሩ አንስተው ይሁን እንጂ ምክርቤቱ ከተመሰረተ በኋላ ግን ስራዎችን ለመስራት የህጋዊነት ጥያቄ እየተነሳባቸው እንዳለ ጠቁመዋል

በአዋጅ እንዳለተቋቋመ  እና ተጠሪነቱ ለዚህ ነው የሚል ሃላፊነት ስላልተሠጠው ከሌሎች ህጋዊ ከሆኑ አካላት ጋር ተንቀሳቅሶ ለመሰራት እንደተቸገረም ተነስቷል።

ለምርጫ ቦርድ እና ለሚመለከተው ህጋዊ ሰወነት እንዲሰጠው ጥያቄ ቢያቀርብም ግንባር ወይም ቅንጅት ወይ ደግሞ ነጠላ ፓርቲ ካልሆናቸው ህጋዊ ሰውነት የማግኘት አግባብ የላችሁም የሚል ከምርጫ ቦርድ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።

ለአለም አሰፋ
ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply