የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሽግግር ፍትህ ተፈፃሚነቱ ላይ እምነት እንደሌለው ገለጸየፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በሽግግር ፍትህ ተፈፃሚነት ላይ እምነት እንደሌላቸው…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/nUcD2TRk2NZSqP_qCit-3pFvveDt2A1GE42L-_GJfcKJNWq5m_QCFSadXjU_tFasUcgKi70hdezU5echY-w_ON5qjORdIayVQx2Mr8wXginj5rPWg5xH98ZHodXL1zTgKXbEq0NIY2ydoox8_g9R__fUFU_TRucnmdqp3YLJv3757_emC0RhQr-8a5h5QwXCepOEz6nl5GmyORwEgu-2mHhxnYQLu-U1dAEwJ341QZ6fobxxl1ASBzboLETCPEKbId_6nxeLF2LSFtnrn41L_swtweu1_cwbm0I-y0Pc81Lmu5fKVi9HLf3dxf0wUjl-Me76PeqWVdddM6stB1xMbQ.jpg

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሽግግር ፍትህ ተፈፃሚነቱ ላይ እምነት እንደሌለው ገለጸ

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በሽግግር ፍትህ ተፈፃሚነት ላይ እምነት እንደሌላቸው ለጣቢያችን ገልፀዋል::

የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ደስታ ዲንቃ እንዳሉት ፖሊሲው እያረቀቀ ያለው አካል በመንግስት በኩል መሆኑን ጉዳዩ ተዓማኒ እንዳይሆን አድርጎታል ብለዋል::

ሰብሳቢው የሽግግር ፍትህ ዋና አላማው በዳይ እና ተበዳይ እንዲካካሱ እና ሰላም እንዲወርድ የሚያስችል መሆኑን አንስተው፤

ካሳ እና ይቅርታ ጠያቂው አካልስ ማነው አስፈፃሚው አካልስ የሚለው ጥያቄ የሚያስነሳ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

በመሆኑም እነዚህ አይነት ነገሮች ባልተማሉበት ተበዳይን የሚክስ አካሄድ ነው ብለው እንደማያምኑም ገልፀዋል።

የሽግግር ፍትህ ሰነዱ መነሻው መድረሻውም የማይታወቅ ነው የሚሉትአቶ ደስታ ዲንቃ ወጥ የሆነ እና ገለልተኛ ነው ብሎ ማመን እንደሚያስቸግር ገልፀዋል።

የሽግግር ፍትህን ተፈፃሚ የሚያደርግ ልዩ ፍርድ ቤትና አቃቤ ሕግ እንዲቋቋም የሚጠይቅ ረቂቅ ወደ ሚንስትሮች ምክር ቤት ቢላክም ውድቅ መደረጉ የሚታወስ ነው።

ለአለም አሰፋ
ሰኔ 18 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply