የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ያወጣውን መግለጫ ለሽብርተኝነትና ለፀረ ህዝብ ሀይል ድጋፍ የሚሰጥ ነው ያለው አሲምባ በእጅጉ ማዘኑ ገልጾ በፓርቲው ሆነ በትግራይ ህዝብ ዘንድ…

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ያወጣውን መግለጫ ለሽብርተኝነትና ለፀረ ህዝብ ሀይል ድጋፍ የሚሰጥ ነው ያለው አሲምባ በእጅጉ ማዘኑ ገልጾ በፓርቲው ሆነ በትግራይ ህዝብ ዘንድ…

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ያወጣውን መግለጫ ለሽብርተኝነትና ለፀረ ህዝብ ሀይል ድጋፍ የሚሰጥ ነው ያለው አሲምባ በእጅጉ ማዘኑ ገልጾ በፓርቲው ሆነ በትግራይ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት የለውም ሲል ውድቅ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 28 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ መግለጫው የሓገራችንን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ያላስገባ፣ የትግራይ ክልል ሕዝቦችንም ፍላጎትና ትግል ለማጨናገፍ ያለመና በመንግሥት የህግ ማስከበር ስራ ጣልቃ የገባ እንደሆነ ፓርቲያችን የዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በፅኑ ያምናል። በተጨማሪም እኛን ጨምሮ ሌሎች ፓርቲዎች በጉዳዩ ላይ ጥሪ ሳይደረግልንና ጥልቅ ውይይት ሳይደረግበት ይህን አይነት አሳዛኝ ለሽብርተኛና ለፀረ ሕዝብ ሀይል ድጋፍ የሚሰጥ መግለጫ በእጅጉ አሳዛኝ ሆኖ ኣግኝተነዋል። ይህ መግለጫ የጋራ ምክር ቤቱ የጋራ ይሁንታና ተቀባይነት የሌለው የውስን ግለሰቦች ብቻ ፍላጎት የተንፀባረቀበት መግለጫ እንደሆነ በመረዳት ፓርቲያችንም ሆነ የትግራይ ሕዝቦች ውድቅ ያደረጉት መሆኑን እንገልፃለን ብሏል አሲምባ በመግለጫው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply