የኢትዮጵያ ደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት የደም ላጋሾች ቁጥር አሽቆልቁሏል አለ::እንደ ሀገር በ 9 ወር ውስጥ 3 መቶ 15 ሺ ዮኒት ደም ይሰበሰባል ተብሎ ቢታቀድም መሰብሰብ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/nq9muDpSRTIZ4Vheb8-zrtxvmbPr_USZP05AMRZ-_b8mqtLgTT53NoUT_6tmUV8XGeYYkGNTbkaX4lOplcQR1UU4i7uYoj_U5yu4eooVXgb6-5G873krTKx-Vn0ntZ4gDD4AWFLLp4wg4fBkL1osaUrkKMLJXsIFyy8k5krRH9I4s-t8GFaqwG2eEiVNA6xjL04seBfZhoW-ZY1sU-QfBng6hCNsxXe19D2iLDTPMl0OQksGb_kR0LXzSfP7WYCVAr_F58Uwl59ajx3b414w7Mtq7dxPrT0FZmvtlYGo2KP1W7oF6UnGR3UxDQtm5lzlukcOoboTHUuAM2pjB1apMg.jpg

የኢትዮጵያ ደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት የደም ላጋሾች ቁጥር አሽቆልቁሏል አለ::

እንደ ሀገር በ 9 ወር ውስጥ 3 መቶ 15 ሺ ዮኒት ደም ይሰበሰባል ተብሎ ቢታቀድም መሰብሰብ የተቻለው 2 መቶ 48 ሺ ዩኒት ደም ነው ተብሏል፡፡

የተሰበሰበው የደም መጠንም ከታቀደው አንፃር ጉድለት ያለው መሆኑን የኢትዮጵያ ደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

አዲስ አበባ ላይ ብቻ ወደ 96 ሺ ይሰበሰባል ተብሎ ቢታቀድም 68 ሺ የሚሆነውን ማግኘት እንደተቻለ የኢትዮጵያ ደም እና ህብረህዋስ ባንክ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ታዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

እንደ አለም ጤና ድርጅት የአንድ ሀገር የደም አቅርቦት በቂ ነው የሚባለው ቢያንስ ከሀገሪቱ ህዝብ 1 በመቶ የሚሆነው ደም ሲለግስ መሆኑን ያስቀምጣል ብለዋል፡፡

ይህም ማለት በአመት አንድ ሚሊዮን ሰው ደም መለገስ ይጠበቅበታል ማለት ነው ሲሉ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

የህክምና ተቋማት እየሰፉ የመጡበት እና የደም ተጠቃሚው ማህበረሰብ እየተበራከተ በመሆኑ ያንን ፍላጎት ለሟሟላት እየተሰበሰበ ያለው ደም በቂ አለመሆኑን አንስተዋል፡፡

አዲስ አበባ ከተማም የህክምና ተቋማትን ሙሉ ፍላጎት ለሟሟላት በቀን ቢያንስ 400 ዮኒት ደሞችን መሰብሰብ ይጠበቅብናልም ብለዋል ፡፡

ነገር ግን አሁን ላይ እየተሰበሰበ ያለው የደም መጠን የታቀደውን ያህል የሚገኝባቸው ቀኖች ውስን መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍ እና ደም ህይወት አድን የህክምና ግብአት በመሆኑ ማህበረሰቡ በመልካም ፍቃደኝነት ደም እንዲለግስ የሚል መልእክታቸውንም አቶ ሀብታሙ አስተላልፈዋል፡፡

ሐመረ ፍሬው
ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም

ኤትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጲያዊያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply