የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማኅበር 35 ኛ ዓመታዊ ጉባኤውን ሊያካሄድ መሆኑ ተገለፀ።በ 1981 ዓ.ም የተመሰረተው የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማኅበር 35 ኛ ዓመታዊ ጉባኤውን ሁሉን አቀፍ የጤና…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/TDpqTzpejmq1UxSauWp-AJadX2Ba6hbtqd39kRiCdqFesnMLObL5upvJH0LoYp3yOGZN56Jmd8axRz9k_pfFLLq731CdAIzoZ_hrU0Eqakz2ik9tiZo6R-7QZ5HUUZdS9pRBz8B_UXV2VOHievIpYFSpPBx5m8rT4iw08GJ7UuJUH-LE060jfWnrCt5alI9UAhWq0GC6ocBmAEzCq0PYmKhajkquXCZb-rst350UhAXH93xax0mhFflgeOtnGVRs9ZfP4_UVCiCqfvHbqtAu_NVL1mHd7croxaTDRNreKy2QEZ60AbjlDdFmUmoVtQpgpnhn8PAXHC-DGd7Fm5_ROQ.jpg

የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማኅበር 35 ኛ ዓመታዊ ጉባኤውን ሊያካሄድ መሆኑ ተገለፀ።

በ 1981 ዓ.ም የተመሰረተው የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማኅበር 35 ኛ ዓመታዊ ጉባኤውን ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋን በሚል የትኩረት አቅጣጫ ከመጋቢት 8-10 እንሚያካሄድ ማህበሩ አስታውቋል።

የዘንድሮ አመታዊ ጉባኤ ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋን ዋና ጭብጥ ላይ የሚያተኩር በመሆኑ ለመሰረታዊ ጤና አገልግሎት ተደራሽነትና ሽፋን ትግበራ ጉልህ ድርሻ እና ወሳኝ ግብአት እንደሚኖረው የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማህበር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለማየሁ መኮንን አንስተዋል።

ለሶስት ቀናት በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ በርካታ የጤና ባለሙያዎች እንደሚሳተፉ እና የተለያዮ የጥናት ውጤቶች እንደሚቀርቡ ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

በጉባኤው በዓመቱ ዋና እና ንዑስ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያም የፓናል ውይይት ይደረጋል ተብሎም ይጠበቃል።

ማኅበሩ ከ 9,000 በላይ በልዩ ልዩ የጤና ዘርፍ የተሰማሩ አባላትን አቅፎ የያዘ ሲሆን ከመንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

በሀገራችን የጤና አገልግሎት ጥራት መሻሻል ብሎም የጤና ልማት ላይ እያደረገ ያለው አስተዋፅኦም ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል::

በጉባኤው ከ 800 -1000 የሚሆኑ በጤናው መስክ በርካታ ልምድ ያካበቱ ባለሙያዎች የሚሳተፉ ሲሆን በዚሁ አጋጣሚ ለማሕበሩ አባላት እንዲሁም አጋር ድርጅቶችና ባለድርሻ አካላት በጉባኤው ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የሚል ጥሪያቸውን ዶ/ር አለማየሁ መኮንን አስተላልፈዋል።

በሐመረ ፍሬው

መጋቢት 03 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply