የኢትዮጵያ ጦርነት የፕሬስ ነፃነትን ይበልጥ አዳክሟል

https://gdb.voanews.com/63195813-FF55-41CB-9B26-EC9FFDE406E8_cx10_cy1_cw89_w800_h450.jpg

ኢትዮጵያ ውስጥ የተካሄደው ጦርነት “የመገናኛ ብዙኃን ነፃነትን ይበልጥ ሸርሽሮታል” ሲል ለጋዜጠኞች ደኅንነት የሚሟገተው ሲፒጄ ትናንት አስታውቋል።

ሲፒጄ በዚሁ መግለጫው “ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከአራት ዓመታት በፊት ወደሥልጣን ሲወጡ መሻሻል አሳይቶ የነበረው የመገናኛ ብዙኃን ነፃነት ይዞታ በጥቅምት 2013 ዓ.ም. በፌዴራል መንግሥቱና በትግራይ አማፂያን መካከል ጦርነት ከተጫረ ወዲህ አሽቆልቁሏል” ብሏል።

ጦርነቱ ከተቀጣጠለ ወዲህ 64 የሚዲያ ባለሙያዎች መታሠራቸውን ዋና ፅህፈት ቤቱ ዩናይትድ ስቴትስ የሆነው ተሟጋች ቡድን ጠቁሟል።

ካለፈው ዓመት ኅዳር ወዲህ 16 ጋዜጠኞች መታሰራቸውንና ያነሳው ሲፒጄ “ይህም ኢትዮጵያን ጋዜጠኞችን በማሰር ከሰሃራ በስተደቡብ ካሉ ሃገሮች ቀዳሚ ከሆችው ኤርትራ ጋር ያተካክላታል” ብሏል።

አሁን ስምንት ጋዜጠኞች ታስረው እንደሚገኙ ቡድኑ አክሎ አመልክቷል።

“በዚህም – ይላል ሲፒጄ – ኢትዮጵያ ሃሣብን በመግለፅ ነፃነት ሠንጠረዥ ላይ 40 ደረጃ ዝቅ እንድትልና ከ180 ሀገሮች ወደ 140ኛ ደረጃ እንድትወርድ አድርጓታል” ብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply