የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የፌዴራል ተቋማትን ለመጠበቅ መቀሌ ገብቷል።በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት መሠረት በመንግስት የሚተዳደሩ ተቋማትን ለመጠበቅ የኢትዮጵያ ፌደዴል ፖሊስ በዛሬው ዕለት ትግራይ ክ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/OP3lz-A0MnJYHxZ8kvxtIi1UG9oHEfewu4KTpV_KVHmefIX4PQdJgMxIjT6A3cnKaonB4lZWGVyeWpPxqnOzQQQibuIuyhJD7FJjuRseznAZRLYsobKh32xfxBvIYldR6FBTk9uG2w1uDjyAxfRB49bzJREOL-el5D5U7r5j0NJLZan_oN-Ay6Uf37WaSbF5ovEdRf86y4mOctsu7OUsYueBsYPllBXV4X3NLflPprk-srys814VPquFdoULQO8YteJBx_SeSdqdOkkw-XBHPbCJ9ewdODorfS6ke8SIQ7uYnYpuXYERbjUyvfoLRospr2Br7M7aXWAhG5yR9Ti1NQ.jpg

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የፌዴራል ተቋማትን ለመጠበቅ መቀሌ ገብቷል።

በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት መሠረት በመንግስት የሚተዳደሩ ተቋማትን ለመጠበቅ የኢትዮጵያ ፌደዴል ፖሊስ በዛሬው ዕለት ትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ገብቶ ሥራ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

ፌዴራል ፖሊስ መንግስትና ህወሓት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የደረሱባቸውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በትግራይ ክልል የሚገኙ በኢፌዴሪ መንግስት የሚተዳደሩ ተቋማትን ለመጠበቅ ነው መቀሌ የገባው፡፡

በዚህ መሰረትም ፌዴራል ፖሊስ በአውሮፕላን ማረፊያዎች፣ በኤሌክትሪክ ኃይል፣ ቴሌኮም አገልግሎት፣ በባንክና ሌሎች ለህብረተሰቡ አገልግሎት በሚሰጡ የፌደራል ተቋማት አስተማማኝ ጥበቃ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply