የኢትዮጵያ ፕላስቲክ እና ጎማ አምራቾች ማህበር ፕራይም ኢትዮጲያ የተሰኘ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል፡፡ፕሮጀክቱ ዙርፉን ለማነቃቃት እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ትስስር ለመፍጠር ዓላማ ያደረገ መሆኑ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/fQr_LDSzWwtG6apZTvdq9JV2mQb2MG3REffg8VhBe9gU9yYMy2dXLgFKuUMspdTC5ZL7PcMaTv-D2w4PTguOEkhz6K6otODN46ccih7mRpx4oMFB44VG8oeJCMTDOINekriWN_fYHbPOuiWXqgLfOjzVj3hF1p1kvY3B5d5HDbppc06zKdcQ8BeytkWGrpC2f4g31CwtHtUUBqVe5ToTtpVgb6Cc1adcz4O0dFpCRn3-DkpXyV89i6fTI41G_ogu2oCpR85kaqVF-MsyhUz4RLYnaSyoP1g1LcKJ-sWcT5oHWYTKne14bim9EyqcXR-tCAmxmSxK2V9-eKL-CpAhdA.jpg

የኢትዮጵያ ፕላስቲክ እና ጎማ አምራቾች ማህበር ፕራይም ኢትዮጲያ የተሰኘ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል፡፡

ፕሮጀክቱ ዙርፉን ለማነቃቃት እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ትስስር ለመፍጠር ዓላማ ያደረገ መሆኑም ታውቋል፡፡

ማህበሩ በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝም ገልጧል፡፡
ማህበሩ ፕሮጀክቱን ይፋ ባደረገበት ወቅት እንዳስታወቀው፣ በ2016 በጀት አመት ኢንዱስትሪውን በአለም አቀፍ መድረክ ማስተዋወቅ እና በውጭ ከሚገኙ ማህበራት ጋር በቅንጅት የመስራት አቅድ መያዙንም ይፋ አድርጓል፡፡

በተጨማሪም ፕራይም ኢትዮጵያ በተሰኘው ፕሮጀክት ላይ ከሚከወኑ ጉዳዮች መካከል በዘርፉ ያሉ ኡንዱስትሪዎች የሚተዋወቁበትን መድረክ መክፈት አንዱ ሲሆን በተጨማሪም አምራቾች የቴክኒክ ሽግግር እንዲያገኙ ውይይቶች እና ወርክ ሾፕች እንደሚያዘጋጅ አስታውቋል፡፡

በዚህ ማህበር ውስጥ 46 የሚደርሱ የፕላስቲክ እና ጎማ አምራቾች የሚገኙ ሲሆን፣ማህበሩ የመረጃ እና የድጋፍ አገልግሎት የሚሰጣቸው 499 አባላት እንዳሉም ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል፡፡

በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኬሚካል እና ኮንስትራክሽን ግብአቶች ኢንዱስትሪ ልማት ምርምር ማዕከል፣የፕላስቲክ እና ጎማ የዘርፍ ሃላፊ የሆኑትን ዶ/ር ዮናስ አባተ፣ ዘርፉ ኢትዮጵያ ነዳጅ አምራች ሃገር ባለመሆኗ እና የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንዳለባት ሃገር፣ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ባንኮች ብድር ሲፈቅዱ በተለየ መልኩ ለአምራቾች ቅድሚያ ቢሰጥ፣ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ከማጠናከር ባሻገር አቅርቦትን በሃገር ውስጥ ምርት ለመተካት ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ብለዋል፡፡

በረድኤት ገበየሁ

Source: Link to the Post

Leave a Reply