የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ 4ተኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን አደረገ።

ሚያዝያ 17/2016 ዓ.ም በሂልተን ሆቴል የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ 4ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን አድርጓል።

በዛሬው መርሃ ግብር ሁለት አጀንዳዎች ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በመጀመሪያው ምዕራፍ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ሪፖርት ዳሰሳ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ክለብ ላይሰንሲንግ ዳይሬክተር አቶ አምሃ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በመቀጠል የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የክፍያ ስርዓት አስተዳደር መመሪያ በአከሰሲዮን ማህበሩ ም/ቦርድ ሰብሳቢ ረ/ፕ ጌቱ ደጉ ቀርቦ ሰፊ ወይይት ተደርጎበታል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የክፍያ ስርዓት አስተዳደር መመሪያ በዋናነት የተዘጋጀው አክሲዮን ማህበሩ ያሰጠናውን የዳሰሳ ጥናትን ተከትሎ ሲሆን በውስጡ የአፈፃጸም ሂደቶች፣ የፋይናንስ አሰተዳድር ቁጥጥር አደረጃጀት እና ሌሎችም ተያያዥ አርዕስቶችን ይዟል።

ክለቦች መመሪያው ላይ ሃሳብ ከሰጡበት በኋላ በሙሉ ድምፅ አፅድቀውታል።

በፋይናንስ አሰተዳደር ሰነዱ ዙሪያ አዘጋጆቹ የቦርዱ አባላት በከሰዓቱ መርሃ ግብር ለተገኙ የስፖርት ጋዜጠኞች – ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። ከጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቂዎችም ምላሽ ሰጥተዋል።

በጋዲሳ መገርሳ
ሚያዝያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply