የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችንን ይከታተሉ፦በዛሬው የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ( ከ1:00-2:30)- በኦሮሚያ ክልል በቄለም ወለጋ ዞን ውስጥ የሚገኙ ንጹሀን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/cERYbbFP_qUhdecnx6NjYMcm7x4netI_p0RF26hwVupDX5U3ZuFgeAZBzD3SZIk_T68RwWgg8w2ipjJAdtTwOPffPLtV7rS4DBbkLh8b5--UT8Vo4Tntom5jStpK1y19ExV6tFyqpvIUsiCqMWCVIUdm8iIzlFDEEUjZZmNJq06JzYeXGwzhim51ksOYZ0klArSQdefBJ3JLDjkESY_FAsPueEI6ZTmvBuo-1r6TpGmursNDpY3lJVdPEG4p4El2kWFUOBulNhNHtmulOWpKLs4xbYrbBBvU6oQOrte-QcJ33Gm6eg3Q_hOqlDwdieVsROf1Q4vPvgHkJOKDKqLFWQ.jpg

የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችንን ይከታተሉ፦

በዛሬው የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ( ከ1:00-2:30)

– በኦሮሚያ ክልል በቄለም ወለጋ ዞን ውስጥ የሚገኙ ንጹሀን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ በተመለከተ ሰፋ ያለ መረጃ ይዘናል

-ኢትዮጵያ የበርበራ ወደብን እንድታጣ የኃያላን አገራት ግፊት በግልጽ እየተስተዋለ ነዉ።

ኢትዮጵያ የወደብ አማራጭ እንዳታገኝ የሚሰራዉ ሴራ አሁንም ቀጥሏል።

ሱማሊላንድም ኢትዮጵያ በበርበራ ወደብ ላይ የነበራትን ድርሻ እንዳጣች ከሰሞኑ ገልጻለች፤
ለመሆኑ ኢትዮጵያ የበርበራ ወደብን እንድታጣ የሚያደርጉ ገፊ ምክንያቶች ምንድናቸዉ?

ወቅታዊው የአፍሪካ ቀንድ የሃይል አሰላለፍስ እንዴት ይታያል ስንል ምሁራንን አነጋግረን ዝርዝር ዘገባ አዘጋጅተንላችኋል።

– አሁንም አንገብጋቢ ጉዳይ ሆኖ የቀጠለው ነዳጅና በዚሁ ምክንያት የስርጭት ሰዓት ከመቀነስ እስከ ስርጭት ማቋረጥ የደረሰ ስጋት ተደቅኖብናል ስላሉት የሬዲዮ ጣቢያዎችም በዜናችን ተዳሰዋል።

-በሰሜኑ ጦርነት ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገደው የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ አሁን በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል? ስንልም ጠይቀናል።

– ድሯችንና ቢዝነስ ቲብስ የተሰኙ ጥንቅሮችም አሉን።

– እንዲሁም ሌሎች አዳድስ የሀገር ውስጥና ዓለምዓቀፋዊ ጉዳዮችንም አሰናድተንላችኋል፤

የቻላችሁና የፈቀዳችሁ እንድታደምጡ ተጋብዛችኋል።

ለአስተያየትዎ ‘6321’ አጭር የጽሁፍ መልዕክት

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply