የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችንን ይከታተሉ፦በዛሬው የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ( ከ12:30-2:30)-ከቤት ሳንወጣና ስፖርታዊ ጉዳዮችን ትሰማላችሁ- በመንገዳችን ላይ፦በአዲስ አበባ በተለያዩ…

የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችንን ይከታተሉ፦

በዛሬው የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ( ከ12:30-2:30)

-ከቤት ሳንወጣና ስፖርታዊ ጉዳዮችን ትሰማላችሁ

– በመንገዳችን ላይ፦በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች የዘመሙ የኤሌክትሪክ ሀይል ተሸካሚ እንጨቶች በተለይም በህጻናት እና አረጋዊያን ህይወት ላይ አደጋ ደቅነዋል፤ ለምን? ከጥንቅሩ ትሰሙታላችሁ።

– ለጤናችን፦ በታሸጉ ምግቦች ውስጥ የሚገኘው ትራንስ ፋቲ አሲድ ብዙዎችን ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች እየዳረገ ይገኛል።

መፍትሄው ምን ይሆን? የባለሙያ ምክረ ሀሳብ ይዘንበታል።

– በፍተሻ ሰዓታችን፦ ሩሲያና አሜሪካ ኢትዮጵያን የግላቸው ለማድረግ በዛሬው ዕለት ይፋዊ ዘመቻ ይጀምራሉ።

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ።
የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛም በተመሳሳይ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ።

ሁለቱ አገራት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያን ለምን መረጡ?

በዚህ ጉዳይ የህግና የፖለቲካ ባለሙያዎችን አስተያየት እንዲሁም የኤምባሲዎችን ምላሽ አካተናል፤ ጉዳዩን ፈትሸነዋል።

-በኢትዮ ገበያችን ፦
በከፍተኛ የዋጋ ንረትና በውጭ ምንዛሬ እጥረት እየተጨነቀች ለምትገኘው ሀገራችን ኢትዮጵያ መተንፈሻ መፍትሄው ይህ ነው ሲል የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን ጥናቱን ይፋ አድርጓል፤ ትሰሙታላችሁ።

-በዓለም ጉዳይ፦ በቱኒዝያ ህዝቡና መሪዋ የተለያየ ጉዞ ጀምረዋል።

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ካይስ ሰኢድ ስልጣናቸውን ለማስጠበቅ ህገ መንግስቱ ይሻሻል እያሉ ነው፤
ብዙሀኑ ቱኒዚያዊያን ግን ይህን አይፈልጉም።

ህዝብና መንግስት በዚህ ልዩነት ውስጥ ሆነው ህገ መንግስቱን ለማሻሻል ድምጽ መስጠት ተጀምሯል፤ በትንታኔ አዘጋጅተንላችኋል።

-በኮሮና ቫይረስ የተጠቁት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ማገገማቸው ተነግሯል።

– በሳውዲ ዓረቢያ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ተጠቂዎች ተገኝተዋል።

– እንዲሁም ሌሎች አዳድስ የሀገር ውስጥና ዓለምዓቀፋዊ ጉዳዮችንም አሰናድተንላችኋል

እንድታደምጡ ተጋብዛችኋል።

ለአስተያየትዎ ‘6321’ አጭር የጽሁፍ መልዕክት

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply